በኢትዮጵያ የመስከረም ወር አገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት መጠን 13.2 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል።
ይህ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ነሐሴ ወር ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን፣ በነሐሴ ወር 13.6 በመቶ ሆኖ ተመዝግቦ የነበረው መጠን በመስከረም ወር ወደ 13.2 በመቶ ዝቅ ብሏል።
በመስከረም ወር ከተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ውስጥ የምግብ ነክ ዕቃዎች (Food Items) የዋጋ ግሽበት 12.1 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) የዋጋ ግሽበት ደግሞ 14.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።


