የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) የባለሞያዎች ቡድን በአልቫሮ ፒሪስ መሪነት ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር ፋሲሊቲ መርሃግብር በአራተኛው ግምገማ ላይ በባለሞያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቋል።
ይህ ስምምነት በአይኤምኤፍ ቦርድ ሲጸድቅ፣ ቀጣዩ የ261 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ለኢትዮጵያ የሚለቀቅ ሲሆን፣ ይህም በአጠቃላይ የተሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ወደ 2.13 ቢሊዮን ዶላር ያደርሰዋል።
አይኤምኤፍ በኢትዮጵያ የማክሮ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ስር ከፍተኛ የእድገት እና የኤክስፖርት መሻሻል መኖሩን ጠቅሶ፣ ነገር ግን የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማስጠበቅ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ እንዲቀጥል እና የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማሻሻል ተጨማሪ እርምጃዎች እንዲወሰዱ አሳስቧል።
በተጨማሪም፣ በG20 የጋራ ማዕቀፍ ስር የዕዳ መልሶ ማዋቀር ጥረቶች እየገፉ መሆናቸውና ከኦፊሴላዊ አበዳሪዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ ተገልጿል። Seco


