Tag: Teleplay
ኢትዮ ቴሌኮም ለቴሌፕሌይ ጨዋታ አሸናፊዎች ቢዋይዲ መኪኖችን ሸለመ
ዛሬ በመስቀል አደባባይ መገናኛ ብዙሃን በተከታተሉት የዲጂታልዕጣ መርሃ ግብር ሶስት የተለያዩ ቁጥሮች ዕድለኛ የስልክ ቁጥር ሆነው ወጥተዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ዕጣው ከደረሳቸው ሰዎች ስልክ ተደውሎላቸውለተገኙት ሁለት ዕድለኞች በቀጥታ መሸለማቸውንአብስሯቸዋል፡፡
ኩባኒያው ለአንድ ዓመት ያክል ባካሄደው የቴሌፕሌይ ጨዋታኤሌክትሪክ መኪኖቹን ሳይጨምር በየቀኑ፣ በየሳምንቱና በየወሩከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብ፣ የጉዞ፣ የሞባይልቀፎና የቴሌኮም አገልግሎት ሽልማት አበርክቷል።
ለአንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሰዎች የስልክ ቀፎ፣ ለሁለት መቶ አርባሁለት ሺህ ደንበኞች ደግሞ ገንዘብ ተላልፏል፡፡ ሁለት ሚሊየንየሚጠጉ ተሳታፊዎች የኩባኒያው የተለያየ ዐይነት አገልግሎትደርሷቸዋል፡፡
የጨዋታው ዓላማ ቴክኖሎጂ አፍቃሪያን እየተዝናኑክህሎታቸውንና ያላቸውን እምቅ ተሰጥኦ እንዲጠቀሙ ማስቻልመሆኑን የኩባኒያው የስትራቴጂክ ፓርትነርሺፕና ሰፖርትዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን መክብብ አስታውቀዋል፡፡
በዚህም ልዩ ልዩ ፈጠራ የታከለባቸውን ሀገር በቀል የቴክኖሎጂውጤቶች እያቀረበ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
እንደሳቸው አባባል ይህ አዝናኝ ጨዋታ ዕድለኞችን ከመሸለምባሻገር ሀገራችን አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመዘርጋትና ለአካባቢ ጥበቃየሚስማማ የመጓጓዣ ስርዐት ለማስፋት የምታደርገውን ሽግግርየማበረታታትና የመደገፍ ተልዕኮም አለው።
ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ቢ ዋይ ዲ መኪኖች በዕጣ ለወጣላቸውእድለኞች በቀጣይ በሚዘጋጅ ልዩ የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብር በይፋ እንደሚያስረክባቸው አስታውቋል፡፡
የዕጣውን ሂደት የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች፣መገናኛ ብዙሃንና ተጋባዥ እንግዶች ተከታትለውታል፡፡
አቶ ሚሊዮን የቴሌፕሌይ መዝናኛና ሽልማት ይቀጥላል ብለዋል፡፡ደንበኞቹ በጨዋታው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ዕለታዊ፣ሳምንታዊና ወርሃዊ ሽልማት ለማሸነፍ እንዲተጉ ጥሪአቅርበዋል።
አቶ ሚሊዮን የመኪና ሽልማቱ ከእንግዲህ በኋላ በየሶስት ወሩእንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም የመጪውን ዘመን የቴክኖሎጂና የዲጂታልትስስር ታሳቢ ያደረገ የሶስት ዐመት ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰይገኛል፡፡
ይህ ዕቅድ ደንበኞቹ በኩባኒያው አገልግሎት ከሚጠቀሙትየመረጃ አቅርቦት በተጨማሪ የተለያየ ክህሎት እንዲያጎለብቱያግዛል ያለውን ስልት የሚያስፈጽምበት ነው፡፡
በቴሌብር በመገበያየትና በማይ ኢትዮቴሌኮም የአየር ሰዐት ሲገዙለዕድል የሚታጩበት ደረሰኝ ወዲያው ያገኛሉ፡፡
በድግግሞሽ የሚያጠራቅሙት ነጥብ ደግሞ ወደ ዕድለኛነትእንዲጠጉ ያስችላቸዋል፡፡
ይህ ዓይነቱ አሰራር ደንበኞቹ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በክህሎትእንዲጠቀሙና እንዲዝናኑ አጋጣሚውን እንደሚፈጥር ነው አቶሚሊዮን የተናገሩት፡፡
ከኩባኒያው ጋር ያላቸውን ትስስር ለማጠናከርም ያግዛል ብለዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚዎች ቁጥር ከዘጠና ሚሊየንተሻግሯል፡፡ የደንበኞቹም ቁጥር ከስልሳ ሚሊዮን በልጧል፡፡SECO
