ኢትዮ ቴሌኮም ለቴሌፕሌይ ጨዋታ አሸናፊዎች ቢዋይዲ መኪኖችን ሸለመ

ዛሬ በመስቀል አደባባይ መገናኛ ብዙሃን በተከታተሉት የዲጂታልዕጣ መርሃ ግብር ሶስት የተለያዩ ቁጥሮች ዕድለኛ የስልክ ቁጥር ሆነው ወጥተዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ዕጣው ከደረሳቸው ሰዎች ስልክ ተደውሎላቸውለተገኙት ሁለት ዕድለኞች በቀጥታ መሸለማቸውንአብስሯቸዋል፡፡

ኩባኒያው ለአንድ ዓመት ያክል ባካሄደው የቴሌፕሌይ ጨዋታኤሌክትሪክ መኪኖቹን ሳይጨምር በየቀኑ፣ በየሳምንቱና በየወሩከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብ፣ የጉዞ፣ የሞባይልቀፎና የቴሌኮም አገልግሎት ሽልማት አበርክቷል።

ለአንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሰዎች የስልክ ቀፎ፣ ለሁለት መቶ አርባሁለት ሺህ ደንበኞች ደግሞ ገንዘብ ተላልፏል፡፡ ሁለት ሚሊየንየሚጠጉ ተሳታፊዎች የኩባኒያው የተለያየ ዐይነት አገልግሎትደርሷቸዋል፡፡

የጨዋታው ዓላማ ቴክኖሎጂ አፍቃሪያን እየተዝናኑክህሎታቸውንና ያላቸውን እምቅ ተሰጥኦ እንዲጠቀሙ ማስቻልመሆኑን የኩባኒያው የስትራቴጂክ ፓርትነርሺፕና ሰፖርትዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን መክብብ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ልዩ ልዩ ፈጠራ የታከለባቸውን ሀገር በቀል የቴክኖሎጂውጤቶች እያቀረበ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

እንደሳቸው አባባል ይህ አዝናኝ ጨዋታ ዕድለኞችን ከመሸለምባሻገር ሀገራችን አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመዘርጋትና ለአካባቢ ጥበቃየሚስማማ የመጓጓዣ ስርዐት ለማስፋት የምታደርገውን ሽግግርየማበረታታትና የመደገፍ ተልዕኮም አለው።

ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ቢ ዋይ ዲ መኪኖች በዕጣ ለወጣላቸውእድለኞች በቀጣይ በሚዘጋጅ ልዩ የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብር በይፋ እንደሚያስረክባቸው አስታውቋል፡፡

የዕጣውን ሂደት የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች፣መገናኛ ብዙሃንና ተጋባዥ እንግዶች ተከታትለውታል፡፡

አቶ ሚሊዮን የቴሌፕሌይ መዝናኛና ሽልማት ይቀጥላል ብለዋል፡፡ደንበኞቹ በጨዋታው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ዕለታዊ፣ሳምንታዊና ወርሃዊ ሽልማት ለማሸነፍ እንዲተጉ ጥሪአቅርበዋል።

አቶ ሚሊዮን የመኪና ሽልማቱ ከእንግዲህ በኋላ በየሶስት ወሩእንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የመጪውን ዘመን የቴክኖሎጂና የዲጂታልትስስር ታሳቢ ያደረገ የሶስት ዐመት ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰይገኛል፡፡

ይህ ዕቅድ ደንበኞቹ በኩባኒያው አገልግሎት ከሚጠቀሙትየመረጃ አቅርቦት በተጨማሪ የተለያየ ክህሎት እንዲያጎለብቱያግዛል ያለውን ስልት የሚያስፈጽምበት ነው፡፡

በቴሌብር በመገበያየትና በማይ ኢትዮቴሌኮም የአየር ሰዐት ሲገዙለዕድል የሚታጩበት ደረሰኝ ወዲያው ያገኛሉ፡፡

በድግግሞሽ የሚያጠራቅሙት ነጥብ ደግሞ ወደ ዕድለኛነትእንዲጠጉ ያስችላቸዋል፡፡

ይህ ዓይነቱ አሰራር ደንበኞቹ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በክህሎትእንዲጠቀሙና እንዲዝናኑ አጋጣሚውን እንደሚፈጥር ነው አቶሚሊዮን የተናገሩት፡፡

ከኩባኒያው ጋር ያላቸውን ትስስር ለማጠናከርም ያግዛል ብለዋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚዎች ቁጥር ከዘጠና ሚሊየንተሻግሯል፡፡ የደንበኞቹም ቁጥር ከስልሳ ሚሊዮን በልጧል፡፡SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories