የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 220 ቦታዎች ላይ አዲስ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን አስታወቀ። ቢሮው የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ከቀጣዩ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

​የሊዝ ጨረታ የወጣባቸው ቦታዎች በልደታ፣ አዲስ ከተማ፣ ጉለሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ የካ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ለሚ ኩራ፣ ኮልፌ ቀራንዮ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን፤ ቦታዎቹ ለንግድ ወይም ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ለጨረታ የቀረቡት እነዚህ ቦታዎች በአጠቃላይ 7.7 ሄክታር ስፋት ያላቸው ሲሆን፣ ሁሉም ቦታዎች ምንም ዓይነት የይገባኛል ውዝግብ የሌለባቸው መሆናቸውን ቢሮው ማረጋገጫ ሰጥቷል።

​የከተማ አስተዳደሩ በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት ሁለት ዙር የሊዝ ጨረታዎችን ማካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን የቀረበው ጨረታ በዓመቱ ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

በኢትዮጵያ የምግብ ምርቶች ዋጋ ከ19 በመቶ በላይ ጨመረ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው የመስከረም ወር...

Popular Categories