የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው የመስከረም ወር 2019 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14.9 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በዚህም የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 14.8 በመቶ የጨመሩ ሲሆን በዋናነት አትክልት 11.4 በመቶ ፣ ስጋ 22.0 በመቶ ወተት፣ የወተት ተዋፅኦዎች እና እንቁላል 17.7 በመቶ ፣ ፍራፍሬ 18.5 በመቶ፣ ዘይት እና ቅቤ 18.2 በመቶ ስኳር ፣ ማር እና ቸኮሌት 39.8 በመቶ እና ዳቦ እና እንጀራ 8.6 በመቶ ፣ የምግብ ምርቶች 19.1 በመቶ በመጨመራቸው እንደሆነ ተጠቁሟል።
ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 15.1 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት 16.0 በመቶ፣ አልኮል መጠጦችና ትምባሆ 18.2 በመቶ፣ በኮሙዩኒኬሽን 9.6 በመቶ ፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች 15.3 በመቶ ትምህርት 17.8 በመቶ ፣ ጤና 10.9 በመቶ እንዲሁም ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች 17.6 በመቶ ሆነው ተመዝግበዋል።SECO


