አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ

ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጪ በአዳማ ከተማ ደራርቱ አደባባይ ወይም ወደ ወለንጪቲ በሚወስደው መንገድ ላይ ለህዝብ አገልግሎት የገነባውን አራተኛውን እጅግ ፈጣን (Super-Fast) የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ በይፋ ስራ አስጀምሯል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደገለጹት በአራተኛው ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ሥራ የገባው ይህ ጣቢያ፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ እና እጅግ የላቀ ቴክኖሎጂን እንደሚጠቀምና  በተለይም የአውሮፓ ስሪት ለሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (European EV Models) ጭምር አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም አለው።

ከተሽከርካሪዎቹ ዓይነት ጋር ራሱን የሚያጣጥም እጅግ ፈጣን (Super-Fast) ኃይል መሙያ የተገጠመለት እንደሆነም ጨምረው  ተናግዋል።

ስራ የጀመረው  የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያ በአንድ ጊዜ 12 እጅግ ፈጣን (Super-Fast) የኃይል መሙያዎች፤ እያንዳንዳቸውና እስከ 180 ኪሎዋት በሰዓት የሚደርስ የመሙላት አቅም እንዳላቸው  አስታውቀዋል።

 ኩባንያው ቀደም ሲል የገነባቸውን ሦስት ጣቢያዎች ጨምሮ በአጠቃላይ በአንድ ጊዜ ለ60 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን አቅም የፈጠረ  እንደሆነ ተገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም እስካሁን  ወደ ስራ ባስገባቸው ጣቢያዎች ከ284 ሺህ 32 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ማግኘት ችለዋል።

  በዚህም 7,159,066.88 ኪሎዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ጥቅም ላይ መዋሉ ተገልጿል።@SSECO

Related

Boeing Partnership Helps 832 Ethiopian Students Graduate from Pathways to Space Program

Boeing, in partnership with the Future African Space Explorers...

Scientists Identified a Giant Crocodile That May Have Turned Lucy’s World Into a Deadly Trap

A giant crocodile once ruled Lucy’s world, lurking in...

Rice Gene Discovery Boosts Drought Resistance and Grain Yield

Researchers at Chonnam National University (CNU) in South Korea...

Kifiya Eyes Expansion into Four African Markets Following IFC Investment

Ethiopia-based financial technology company Kifiya Financial Technology PLC is...

6G Could Add $1.24 Trillion to Global Economy by 2040, GSMA Says

The global deployment of sixth-generation (6G) mobile networks could...

Popular Categories