የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት ማህበር የ6 ወራት እቅዱን ማሳካት አልቻለም ተባለ

የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክሲዮን ማህበር በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ለማምረት ካቀደው የወረቀት ምርት ማሳካት የቻለው 52.7 በመቶውን ብቻ መሆኑን አስታወቀ። ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ29.3 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ባይሳ ተመስገን ሰኞ ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፤ ለምርቱ መቀነስ ዋነኛው ምክንያት የማሽኖች ብልሽትና ስራ ማቆም መሆኑን ገልጸዋል። ይሁን እንጂ የጥገና ባለሙያዎች ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ማሽኖቹ ተጠግነው በድጋሚ ወደ ስራ መመለሳቸውን ጠቁመዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው ኩባንያው ለተከታታይ ዓመታት ዝቅተኛ አፈጻጸም እያሳየ መሆኑንና አሁን ባለበት ሁኔታ ወደ ኪሳራ እየተቃረበ መሆኑን አስገንዝበዋል። በጥናት የተደገፈ መረጃ እንደሚያሳየው ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ካለው የማምረት አቅም ውስጥ እየተጠቀመ ያለው 43.5 በመቶውን ብቻ ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ መለሰ መና እንደገለጹት፤ ኩባንያው ለሀገሪቱ የኢንዱስትሪ እድገትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ትልቅ አስተዋጽኦ የነበረው ቢሆንም፣ አሁን ላይ ያለው የቴክኖሎጂ ለውጥ በዘርፉ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። በመሆኑም አሰራርን ለማዘመን፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ብክነትን ለመቀነስ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ለወረቀትና ለወረቀት ውጤቶች ምርቶች በየዓመቱ በአማካይ 170 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የምታደርግ ሲሆን፣ በሀገር ውስጥ የሚመረተው የወረቀት ጥሬ ዕቃ (Pulp) አነስተኛ በመሆኑ አብዛኛው ከውጭ የሚገባ ነው።

በወንጂ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክሲዮን ማህበር፤ 70 በመቶው በመንግስት፣ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ባለቤትነት የሚመራ አንጋፋ የኢንዱስትሪ ተቋም ነው።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories