በኮሬ ዞን ለዘጠኝ ዓመታት ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎች ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ጠየቁ

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጀሎ እና ዶርባዴ ከተባሉ ቀበሌያት ተፈናቅለው የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ወደ ቀደመ ቦታቸው ባለመመለሳቸው ለከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መዳረጋቸውን ገለጹ።

ቁጥራቸው 12 ሺህ 182 የሆኑት እነዚህ ነዋሪዎች በ2009 ዓ.ም በአጎራባች የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በደረሰባቸው ጥቃት መፈናቀላቸውን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

​ተፈናቃዮቹ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ እየኖሩ እንደሚገኙ ጠቅሰው፣ ወደ ቦታቸው ለመመለስ ላቀረቡት ጥያቄ መንግሥት እስካሁን ተግባራዊ ምላሽ አልሰጠንም ብለዋል።

ለችግሩ መፍትሔ ያጣነው ሁለቱ አዋሳኝ ክልሎች (ደቡብ ኢትዮጵያ እና ኦሮሚያ) ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

​የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ በበኩላቸው፣ ክልሎቹ ትኩረት አልሰጡም የሚለውን ወቀሳ አይቀበሉትም። ይልቁንም ተፈናቃዮቹን በተያዘው ዓመት ወደ ቀደመ ቦታቸው ለመመለስ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

​አስተዳዳሪው አክለውም የፀጥታ ሁኔታውን አስተማማኝ ለማድረግ በኮሬ እና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች መስተዳድሮች መካከል መግባባት ላይ መደረሱንና ጥምር የሰላም ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመተካት የግንባታ ቁሳቁሶች እየተሰበሰቡ መሆኑንና ከክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መገባቱን ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

እስራኤል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አገሯ እንዳይገባ አገደች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በበረራ ሰራተኛው ምክንያት ወደ...

የፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ በሀገር ውስጥ፣ በአውሮፓ...

ግብፅ በጅቡቲ በወደብና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላትን ተሳትፎ ልታፋጥን ነው  

የካይሮ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን እንደማያስደስት ተነግሯል የግብፅ የልዑካን ቡድን በጅቡቲ ዋና...

Popular Categories