እስራኤል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አገሯ እንዳይገባ አገደች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በበረራ ሰራተኛው ምክንያት ወደ እስራአኤል እያደረገ የነበረውን በረራ ቀልብሶ ተመልሶ አዲስ አበባ ለማረፍ መገደዱ ተገለፀ።

የኢንዶኔዢያ የበረራ ሰራተኛ አባል በመኖሩ ምክንያት ወደ እስራኤል ያመራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ወደ ኋላ እንዲመለስ ተገዷል ነው የተባለው።

ከአዲስ አበባ የተነሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን፣ እስራኤል የኢንዶኔዢያ ዜግነት ያለው የበረራ አባል አሳፍሯል በሚል በአገሯ እንዳያርፍ በመከልከሏ ምክንያት ትላንት ጥቅምት 1 ቀን (እሁድ ማታ) በአየር ላይ እያለ ወደ ኋላ እንዲመለስ መደረጉን በርካታ የዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል።

እስራኤል ከኢንዶኔዢያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሌላት ያስታወሱት የእስራኤል ሚዲያዎች የአገሪቱ ውሳኔ

ከሰሞኑ አንድ የኦማን ፓይለት አውሮፕላኑን ለመከስከስ በማሰብ ረዳቱን በጩቤ የወጋበትን የ«flydubai» ክስተት ተከትሎ የመጣ ጥብቅ ቁጥጥር መሆኑን አስታውሰዋል።

ቻናል 13 እንደዘገበው ከሆነ፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ላይ የነበሩት የበረራ አባላት ዝርዝር ለእስራኤል ተቆጣጣሪ አካላት የተላከው አውሮፕላኑ ጉዞ ከጀመረ በኋላ ነው።

በመሆኑም የሚመለከታቸው የእስራኤል ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑ በአገሪቱ ማረፍ እንደማይፈቀድለት በማሳወቃቸው እሁድ ማታ ይደረግ የነበረው በረራ ተሰርዞ በሌላ የበረራ ቡድን ሰኞ እለት ጉዞው ተደርጓል ነው የተባለው።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories