ግብፅ በጅቡቲ በወደብና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላትን ተሳትፎ ልታፋጥን ነው  

የካይሮ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን እንደማያስደስት ተነግሯል


የግብፅ የልዑካን ቡድን በጅቡቲ ዋና ዋና የወደብ እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማፋጠን የሚያስችል ውይይት ማድረጉ ተገለፀ። ይህ የካይሮ አዲስ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ በወደብ እና በባህር በር ጉዳይ ቀጠናዊ ተፅዕኖዋን ለማስፋት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚኖረውን ጫና አሳስቧል።


የጅቡቲ የወደቦችና ነፃ የንግድ ቀጠና ባለሥልጣን እንዳስታወቀው፣ በአህመድ ኤል-አሳር የተመራው የግብፅ ግዙፉ “አረብ ኮንትራክተርስ” ኩባንያ ልዑክ ከባለሥልጣኑ ሊቀመንበር አቡበከር ኦማር ሀዲ ጋር ተመካክሯል። ውይይቱ በዋናነት በሁለት ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የመጀመሪያው በዓመት 5 ሚሊዮን ኮንቴይነሮችን ማስተናገድ የሚችል አዲስ የኮንቴይነር ተርሚናል ግንባታ ነው።


ሁለተኛው ደግሞ የደቡባዊ ጅቡቲ አካባቢዎችን የሚያገናኝ 90 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው

የ“RN18” መንገድ ኮሪደር ግንባታ መሆኑ ተጠቁሟል።


ይህ እንቅስቃሴ ካይሮ በታህሳስ 2018 ዓ.ም በጅቡቲ ካደረገችው ስምምነት የሚቀጥል ሲሆን፣ የ23 ሜጋ ዋት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ እና የሎጂስቲክስ ማዕከል ግንባታዎችንም ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።

ጅቡቲ የወደብና የሎጂስቲክስ አቅሟን ለማሳደግ የውጭ ኢንቨስትመንት መሳቧ የሚደገፍ ቢሆንም፣ የግብፅ በስትራቴጂካዊ የመሠረተ ልማት አካባቢዎች ላይ መስፋፋት በኢትዮጵያ በኩል በስጋትና በትኩረት እንደሚታይ ባለሙያዎች ይናገራሉ።


ኢትዮጵያ ለአብዛኛው የወጭና ገቢ ንግዷ በጅቡቲ ወደቦች ላይ የምትተማመን በመሆኗ፣ የግብፅ ተፅዕኖ ማደግ ከቀጠናው ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት ጋር ተያይዞ አዲስ የፀጥታና የኢኮኖሚ ስጋት ደቅኗል።


ኢትዮጵያ በ1985 ዓ.ም የኤርትራን መገንጠል ተከተሎ የባህር በር ማጣቷንና የቀይ ባህር መውጫ ታሪካዊ ጥያቄዋን ለማስመለስ ጥረት በምታደርግበት በአሁኑ ወቅት፣ የካይሮ እና የጅቡቲ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ መቀራረብ የቀጠናውን የስልጣን ሚዛን ሊያናጋው እንደሚችል ስጋት እየደቀነ ይገኛል።SECO














Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

እስራኤል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አገሯ እንዳይገባ አገደች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በበረራ ሰራተኛው ምክንያት ወደ...

የፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ በሀገር ውስጥ፣ በአውሮፓ...

አብዱልበር ሸምሱ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ሆነዉ ተሾሙ

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን (ኢማባ) ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አብዱልበር ሸምሱ...

Popular Categories