የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ


በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ) የ2026 የንግድና ልማት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ የእቃና አገልግሎት ንግድ በ4% ያድጋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የዓለም ኢኮኖሚ እድገት ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.9% በ2026 ወደ 2.6% ዝቅ ይላል ተብሏል። የበለፀጉ ሀገራት ኢኮኖሚ በ2025 ከነበረበት 4.7% ዘንድሮ ወደ 4% ዝቅ ይላል።

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በ2025 የዓለም ንግድ ታሪካዊ የሆነውን 35 ትሪሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር። በ2026 የንግድ እሴት መጨመር በኃይል ቀውስ ምክንያት በተፈጠረው የዋጋ ንረት የሚመራ ነው ብሏል አንክታድ ።


ጥናቱ እንዳመለከተው በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ያለው ንግድ ከ2024 ወዲህ ከ20% በላይ የቀነሰ ሲሆን፣ ምስራቅ አፍሪካ ግን ከቻይና እና ከሰሜን አሜሪካ ጋር ያለውን ንግድ አሰፍቷል። የወጪ ንግድ ቁጥጥሮች እና የኢንቨስትመንት ማጣሪያዎች አዳዲስ ተወዳዳሪዎች ወደ ዘርፉ እንዳይገቡ እንቅፋት ሆነዋል ነዉ የተባለው።


የ2020–2025 መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ የበለፀጉ ሀገራት በሴሚኮንዳክተሮች፣ በታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂዎች እና በኤአይ መሠረተ ልማቶች አካባቢ ያሉ የከፍተኛ እሴት ፕሮጀክቶችን 70% ድርሻ ይዘዋል። ድሃ ሀገራት ግን በወሳኝ ማዕድናት ዘርፍ ብቻ በ60% የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንደሚመሩ ተጠቁሟል፤ ሪፖርቱ አክሎ እንዳመለከተው አፍሪካ የዓለምን አብዛኛውን ኮባልት የምታመርት ቢሆንም፣ ከአረንጓዴ የፋብሪካ ሰንሰለት እሴት የምታገኘው ከ1% ያነሰ ነው።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories