የግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ (ጂፒኢ) ቦርድ አቶ ኤርሚያስ እሸቱን ከሕዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ አድቫይዘሪ ቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።
ሹመቱ ኩባንያው ኢትዮጵያውያን በድርጅቱ ከፍተኛ የአመራር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሚናዎች ላይ የላቀ ድርሻ እንዲኖራቸው የሚደረገው ሒደት ትልቅ ማሳያ ነው ተብሏል።
አቶ ኤርሚያስ አሸቱ በፋይናንስ፣ በካፒታል ገበያ እና በቴክኖሎጂ መር ማሻሻያዎች ላይ ከ25 ዓመታት በላይ ያገለገሉና በአመራር እና በተቋማዊ ለውጥ ስራዎች በተለያዩ የአፍሪካ አገራት በመስራት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ ናቸው።


