የማዕድን ሚኒስቴር ሕገወጥ የማዕድን ንግድንና ኮንትሮባንድን ለመግታት በሚል፣ ከክልሎች ወደ መሀል አገር የሚመጣ ማዕድን በአውሮፕላን መጓጓዝ ላይ ገደብ መጣሉን አስታውቋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው ማዕድኑ አቅጣጫ ቀይሮ በኮንትሮባንድ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ለመከላከል ሲሆን፣ ሕጋዊ ኤክስፖርት አድራጊዎች ግን ሚኒስቴሩ በሚያቀርበው ደብዳቤ ድጋፍ ማግኘታቸው ተገልጿል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ ሚኒስቴሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ከወርቅ ውጪ ባሉ ማዕድናት (በተለይ ታንታለም እና ሊቲየም) የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ዕቅዱን ባያሳካም (ከ9 ሚሊየን ዶላር ታቅዶ 8.4 ሚሊየን ዶላር መመዝገቡ)፣ ዋናው ምክንያት በአነስተኛ ማዕድን አውጪዎች የአቅርቦት መቋረጥ መሆኑን አስረድቷል።
በተጨማሪም በሰቆጣ የከርሰ ምድር ውሃ ፍለጋ ፕሮጀክት ላይም በቦታው ላይ ሰብል በመኖሩ ምክንያት መቀዛቀዝ መታየቱን ሚኒስቴሩ ገልጾ፣ የሎጂስቲክስና የፋይናንስ ውስንነቶች የዘርፉን አጠቃላይ እድገት እያደናቀፉት መሆኑን አብራርቷል ሲል የዘገበው ካፒታል ነዉ።


