ሱዳን ለኢትዮጵያ የምትከፍለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዕዳ ክፍያ አቋረጠች

እዳው ከ90 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል

ከ90 ሚሊዮን ዶላር በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እዳ ያለባት እና በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን፤ በአንድ ዓመት ከ6 ወር እዳዋን ለመክፈል ተስማምታ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ማቋረጧን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

ወደ ጦርነት ከመግባቷ በፊት ከኢትዮጵያ ጋር የሀይል ሽያጭ ስምምነት የተዋዋለችው ሱዳን ከሁለት ዓመት በላይ ባስቆጠረው ጦርነት እዳዋን መክፈል እንዳልቻለች እና ትወስደው ከነበረው ከ120 ሜጋ ዋት ወደ 10 እና 20 ሜጋ ዋት የኃይል ፍጆታዋ ዝቅ ማለቱ መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ያለባትን እዳ ለመክፈል ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር የመክፈያ ቀን ድርድር አድርጋ በ1 ዓመት ከ6 ወር እንድታጠናቀቅ የጊዜ ገደብ ቢሰጣትም 1 ሚሊየን ዶላር ብቻ ከፍላ ሂደቱ መቋረጡን የኃይል መስሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውኛልሲል  አሐዱ ዘግቧል፡፡

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories