አዲሱ M-PESA ለሁሉም መተግበሪያ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በቀላሉ ለማቅረብ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ደንበኞች መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር እና አፕ ስቶር በቀላሉ በማውረድ፣ በማንኛውም ስልክ ቁጥራቸው እና የብሔራዊ መታወቂያ መረጃቸው በመመዝገብ አገልግሎቱን ማስጀመር እንደሚቻል ካምኒው አስታውቋል፡፡
M-PESA ለሁሉም ገንዘብ መላክ እና መቀበል፣ የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣የአየር ሰዓት መግዛት፣ QR code ስካን በማድረግ መክፈል፣ ከ እርፍ በM-PESA የአጭር ጊዜ ብድር መውሰድ እና ከባንክ እንዲሁም ከሌሎች የሞባይል ዋሌቶዎች ገንዘብ ማስተላለፍ ያስችላል ተብሏል።


