በቅርቡ ወደ ባንክ ያደገው ስኬት ባንክ ትርፍ ቅናሽ አሳየ

በኢቢቪ ሪፖርተር

የቀድሞው አዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ወደ ባንክ ካደገ ካለፈው አመት ወዲህ ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ ቢሆንም ያለፈው አመት ትርፉ ከቀዳሚው አመት አንጻር ቅናሽ ማሳየቱ ታውቋል፡፡

ባለፍ ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው ስኬት ባንክ በ2017 የፋይናንስ አመት የተጣራ ትርፉ 1.24 ቢሊየን ብር መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

ሆኖም ይህ ትርፍ ከቀደመው አመት አንጻር የ 300 ሚሊየን ብር ወይም 19 በመቶ ቅናሽ የታየበት ነው፡፡

ስለትርፍ ቅናሽ ምክንያት በባንኩ የተባለ ነገር ባይኖርም በፋይናንስ ዘርፉ መሰል የትርፍ ቅናሽ የተለመደ አይደለም የሚሉት ባለሞያዎች በተለይ የባንኩ የትርፍ ቅናሽ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በተደረገበት አመት መሆኑ ይበልጥ አስገራሚ ነው ሲሉ ነው የገለፁት፡፡

እንዲያም ሆኖ ባንኩ በ2017 የፋይናንስ አመት በብዙ መለኪያዎች የተሻለ አፈጻፀም ማስመዚገቡ ነው የተገልፀው፡፡

ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9.4 ቢሊዮን ብር መድረሱ ታውቋል፡፡

ባንኩ በ2017 በጀት ዓመት ጠቅላላ የሃብት መጠኑን 19.3 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን የተከፈለ የካፒታል መጠኑን ከ6.9 ቢሊዮን ብር ወደ 7.84 ቢሊዮን ብር አሳድጓል፡፡

የደንበኞቹ ቁጥር ወደ 615 ሺህ ማድረስ መቻሉ ተጠቅሷል፡፡ ©SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories