የአማራ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 655 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ

የባንኩ ባለአክስዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) እንደገለጹት ባንኩ በ2017በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 655 ሚሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ85 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ እንደሆነ ገልጸዋል።

 ባንኩ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን በ26 በመቶ በማሳደግ ወደ 31.5 ቢሊዮን ብር ከፍ ማድረጉ ተጠቁሟል።

የባንኩ አጠቃላይ ገቢ በ29 በመቶ በማሳደን ወደ 5.6 ቢሊዮን ብር መጨመር መቻሉንም ነው ዋና ሥራ አስፈፃሚው ያስታወቁት።

ባንኩ ጠቅላላ ሀብት 43 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀ የ23.2 በመቶ ጭማሪ ማሳያት ችሏል፡፡

የባንኩ የብድር ክምችት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ29 በመቶ በማሳደግ ወደ 25.5 ቢሊዮን ብር ማሳደግ እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories