ኢትዮ ቴሌኮም እና ሚኒስቴሩ አምራቾችን የሚያገናኝ “ኢ-ታምርት” የተሰኘ የኢ-ኮሜርስ ፕላትፎርም አስጀመሩ

ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አምራች ኢንዱስትሪዎችን እርስ በርስ የሚያስተሳስር እና ወደ ዲጂታል ግብይት የሚያሸጋግር “ኢ-ታምርት” የተሰኘ ዘመናዊ የንግድ ለንግድ (B2B) የኢ-ኮሜርስ ፕላትፎርም ሥራ ማስጀመራቸውን አስታውቀዋል።

 የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለጹት፤ ፕላትፎርሙ ለአምራቾች የግብዓት አቅርቦት ችግርን በመቅረፍ፣ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ምርቶቻቸውን ለሀገር ውስጥ እና ለአፍሪካ ገበያ እንዲያቀርቡ ያስችላል።

 አቶ መላኩ፣ በዘመናዊ የግብይት ሥርዓት ያልተደገፈ አምራች ኢንዱስትሪ ውጤታማ እንደማይሆን ጠቅሰው፣ ኢ-ታምርት የማምረት አቅምን በማሳደግ፣ ፈጠራን በማበረታታት እና የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማረጋገጥ ረገድ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው አብራርተዋል።

በአጠቃላይ ኢ-ታምርት ኢትዮጵያ ከሸማችነት ወደ አምራችነት ለምታደርገው ሽግግር እና የሀገር ውስጥ ምርቶችን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው የዘርፉ ተወካዮችም አረጋግጠዋል።©SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories