የአፍሪካ ልማት ባንክ ለደቡብ ሱዳን–ኢትዮጵያ-ጅቡቲ ምዕራፍ 2 የትራንስፖርት ኮሪደር 214.4 ሚሊዮን ዶላር አፀደቀ

ከአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን የተቀናሽ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ልዩ አቅርቦት የገንዘብ ድጋፍ ለኢትዮጵያ 181.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ለጅቡቲ 29.71 ሚሊዮን ዶላር እና ለደቡብ ሱዳን 1.96 ሚሊዮን ዶላር  ድጎማዎችን አጽድቋል፡፡

የፕሮጀክቱ ምዕራፍ ሁለት በሦስቱም አገራት ዋና ዋና የመሠረተ ልማት ማሻሻያዎችን እንደሚኖሩት የተገለፀ ሲሆን በዚህም ኢትዮጵያ ውስጥ የ67 ኪሜ የፍጥነት መንገድ ግንባታ እና የዲጂታል የትራንስፖርት ሥርዓቶች ማስፈፀምን ሲያካትት በጅቡቲ በ18 ኪሜ የድኪል-ሙሉድ ክፍል (መስመር) ማሻሻያ ላይ እንደሚያተኩር ነው የተገለጸው፡፡

 በደቡብ ሱዳን ደግሞ የ280 ኪሜ የካፖዬታ-ቦማ-ራአድ መንገድን ለማሻሻል የሚያስፈልጉ ጥናቶችን የማዘመን ሥራ ላይ ይውላል ነው የተባለው።

 በተጨማሪም፣ በኢትዮጵያ 50 እና በጅቡቲ 15 ኪሎ ሜትሮች ተለዋጭ መንገዶች የማሻሻያ የፕሮጀክቱ አካል መሆናቸውንም ባንኩ በድረ-ገፁ አስታውቋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡©SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories