የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሠረት፣ አገሪቱ ወደ ገበያ ተኮር የምንዛሪ ተመን ሥርዓት ከተሸጋገረች ከአንድ ዓመት በኋላ፣ የሀገር ውስጥ የውጭ ምንዛሪ ገበያ በአስደንጋጭ ሁኔታ መከፋፈሉን አመለከተ።
የሪፖርቱ ዋነኛ ግኝት የንግድ ባንኮች ለአንድ የአሜሪካ ዶላር የሚገዙበትና የሚሸጡበት ተመን ላይ ያለው ልዩነት እስከ 15 ብር ድረስ ከፍ ማለቱ ነው። ማኅበሩ ይህ ልዩነት በገበያው ውስጥ ጤናማ ውድድር እና የተቀናጀ አሠራር አለመኖሩን የሚያመላክት ትልቅ ፈተና መሆኑን ገልጿል።
ሪፖርቱ እንደሚያሳየው በ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብር ከአሜሪካ ዶላር አንጻር በ8.1 በመቶ በማሽቆልቆል ከ135.5 ወደ 146.4 ብር ደርሷል። በታኅሣሥ 2018 ዓ.ም ደግሞ የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ከ154 ብር በላይ ሆኗል።
በተጨማሪም በባንኮች የመግዣና የመሸጫ ዋጋዎች መካከል ያለው አማካይ ልዩነት ባለፈው ሩብ ዓመት ከ3.1% ወደ 6.8% ከፍ ብሏል ሲል የዘገበው ካፒታል ጋዜጣ ነዉ። Seco


