የሶማሌላንድ ፕሬዝደንት አብዱራሂም ኢሮ ሰኞ ዕለት በሃርጌሳ በተከፈተው የማእድን አውደ ርዕይ ላይ በተገኙበት ወቅት እንደተናገሩት አገሪቱ ቢበዛ እኤአ በ2027 የነዳጅ ማውጣት ቁፋሮ ትጀምራለች፡፡
መሰረቱን ለንደን ያረገውን ጌኔል ኢነርጂ ጨምሮ በርካታ ነዳጅ አሳሾች የባህር ክልልን ጨምሮ በሶማሌላንድ የነዳጅ ፍለጋ ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡
እንደ ፕሬዝደንቱ ገለጻ ቅድመ ሁኔታዎች በፍጥነት መስመር ከያዙ የቁፋሮ ስራው ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚገባው አዲሱ የጎርጎሮሳውያን 2026 ሊጀመር ይችላል፡፡ ቢዘገይ ግን ከ2027 አያልፍም ሲሉ ነው የገለፁት ፕሬዝዳንት ኢሮ፡፡
የብሪታንያው ጌኔል በፍለጋው ተስፋ ሰጪ ውጤት ማግኘቱ ሲገልጥ ቆይቷል፡፡@Seco


