1.5 ሚሊዮን ዓመታት እንደሚደርስ የተገመተ በጎና መካነ ቅርስ ስፍራ የራስ ቅልና ፊት ተገኘ

በስፒን የሰው ዘር አመጣጥ ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪና ሳይንቲስት ስለሺ ሰማው (ዶ/ር)   ግኝቱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ሆሞ ኢሬክተስ በመባል በሚታወቀው የቅድመ ሰው ዝርያ ጭንቅላትና ፊት  በቨርቹዋል  ዲጂታል ሪኮንስትራክሽን በሳይንቲስቶች መጠናቱን አስታውቀዋል፡፡

ቀደምት የሰው ዝርያዎች ከአፍሪካ ወደ ተለያዩ የአፍሪካና እስያ አህጉራት ያደረጉትን እንቅስቃሴና ኦልድዋን እና አሹሊያ  በመባል በሚታወቁ  የድንጋይ መሳሪያ መጠቀማቸውን በተመለከተ አዲስ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል ፡፡ 

1.5 ሚሊዮን ዓመታት እንደሚደርስ የተገመተውና በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጎና መካነ ቅርስ ስፍራ የተገኘው የራስ ቅልና ፊት በምስራቅ አፍሪካ ከሚታወቁት ከሆሞ ኢሬክተስ ዝርያዎች ጋር ሲወዳደር የተሟላ ገፅታ እንዳለውና ቅሬተ አካሉ የሰው ልጅ ዝርያ ግንድ የሆነው ሆሞ ኢሬክተስ ምንጩ አፍሪካ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብለዋል ፡፡

የጥናቱ ውጤት በቨርቹዋል ሪኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ታግዞ የፊት ገፅታ ምሉእነት የታየበት ሲሆን በአፍሪካ እስካሁን ከተገኙት ተቀራራቢ እድሜ ካላቸው ግኝቶች የመጀመሪያው የተሟላ የራስ ቅልና የፊት አጥንቶች ጥርሶቹን ጨምሮ ለማየት ያስቻለ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የራስ ቅሉና የፊቱ ቅርፅ ከ300,000 አመታት በፊት እድሚያቸው 1.8 ሚሊዮን ዓመታት የሚገመቱና ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን ለቀው ወደ አውሮፓና እስያ ከፈለሱት የቅድመ ሰው ዝርያዎች የጭንቅላትና የፊት ገፅታ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለውም ተናግረዋል ፡፡

አዲሱ ግኝት ሳይንቲስቶች ከ1.8 ሚሊዮን አመታት በፊት ወደ አውሮፓና እስያ የፈለሰውን የቅድመ ሰው ዝርያ ከጊዜ በኋላ ከኤስ ወድ አፍሪካ ተመልሷል የሚለውን መላምት ውድቅ ደረገ መሆኑን ጠቅሰው ሆሞ ኢሬክተስ በአፍሪካ ውስጥ በአዝጋሚ ለውጥ የአሁኑ የሰው ዘር ግንድ መሆኑን ያሳየና ኢትዮጵያም የሰው ዘር መገኛ መሆኗን የሚያጠናክር ግንት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የሆሞ ኢሬክተስ ዝርያ ቀደምት የሆነና ኦልድዋን እና አሹሊያ  በመባል በሚታወቁ  የድንጋይ መሳሪያ መጠቀሙ ዝርያውን ልዩ እንደሚያደርገውና የነዚህ የሁለቱ የድንጋይ መሳሪያዎች ከሆሞ ኢሬክተስ ጋር ባንድ ላይ መገኘታቸው በአርኪዎሎጂ ጥናት እምብዛም ያልተለመደ በመሆኑ የጎናውን ግኝት አስደናቂ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የጎና የፓሊዎአንትሮፖሎጂ ጥናት ፕሮጀክት ባለፉት 30 ዓመታት የምርምር ስራው በአለም ጥንታዊና 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን አመታት ያስቆጠሩ የድንጋይ መሳሪያዎችንና 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን አመታት ያስቆጠረውን አርዲፒተከስ ራሚደስ የተባለውን ጥንታዊ የሰው ዘር ቅሪተ አካል በማግኘት በተለያዩ አለም አቀፍ የሳይንስ ጆርናሎች ላይ አሳትሟል።@Seco   

Related

From Addis Ababa to the U.S. Congress: The Rise of Melat Kiros

In the early hours of July 1, 2026, Melat...

From Construction Mogul to Employee: The Long Road Back to Akir

There was a time when Awotaheign Kiros did not...

The Weeknd Sets $1.3 Billion Tour Record

The Ethiopian born Canadian music star The Weeknd has broken...

She Lost Everything. She Chose to Stand. The Extraordinary Story of Ruth Yirgalem

There is a moment in the 73rd Miss World...

Popular Categories