ብሔራዊ ባንክ የወርቅ ጥራትን ለመለየት ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሊሸጋገር ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከወርቅ አቅራቢዎች በሚረከበው ወርቅ ላይ የባዕድ ነገሮች መቀላቀል በስፋት መስተዋሉን ተከትሎ፣ የጥራት መለኪያ ዘዴውን ወደ ዘመናዊው የ«ስፔክትሮሜትር» ቴክኖሎጂ ለመቀየር መገደዱ ተዘገበ።

ባንኩ እስካሁን ይጠቀምባቸው የነበሩት የዴንሲቲ እና የእሳት ሙከራ ዘዴዎች በኬሚካል ተለውጠው የሚቀርቡ የውሸት ወርቆችን ለመለየት ክፍተት ነበረባቸው ተብሏል።

ይህ ችግር በስፋት የሚስተዋለው በትግራይ ክልል ሽሬ በሚገኘው የግዢ ጣቢያ ሲሆን፣ ባንኩ ችግሩን ለማጣራት ለበርካታ አቅራቢዎች የሚፈፅመውን ክፍያ ለወራት አግዶ እንደነበር ታውቋል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ ምንም እንኳን ይህ ፈተና ቢኖርም፣ ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ከሽሬ ጣቢያ 19 ቶን ወርቅ የቀረበ ሲሆን ይህም ከፍተኛው የአቅርቦት መጠን ሆኖ ተመዝግቧል።@seco

Related

Ethiopia’s Health Spending Set to Surge 73% by 2030, Driven by Government Investment

-Health-related taxes and the exploration of debt-swaps for health...

New ECMA Chief Grants Licences to Two More Investment Banks, Expanding Capital Market Players

The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA), under its newly...

Top 10 Largest Cities in Sub-Saharan Africa by 2050: World Bank Population Forecast

The World Bank projects major population growth in Sub-Saharan...

Popular Categories