“Invest in Ethiopia 2026፡ High Level Business Forum” ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላትን ዝግጁነት በስፋት እንደሚያሳይ ተጠቁሟል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አራተኛውን “Invest in Ethiopia 2026: High Level Business Forum” መጋቢት 17 እና 18 በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ ነው ያስታወቀው፡፡
በፎረሙ ከሰባት መቶ በላይ የሚሆኑ ዓለም አቀፍ የቢዝነስ መሪዎች፣ ፖሊስ አውጪዎችና አጋር የልማት ድርጅቶች ይሳተፉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቅዳሜ ገበያ ኮሚሽኑ ካወጣው መግለጫ ተመልክታለች።
ፎረሙ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ለማዘመን እየተገበረች ያለውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያ እንዲሁም ያሉትን አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስተዋወቅ፤ አዲስ እና የማስፋፊያ የኢንቨስትመንት ቃልኪዳኖች እንዲገቡ አላማ አድርጎ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።
በሀገሪቱ በኢንቨስትመንት መስክ የተለዩትን የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ ፣ግብርና ፣ አይሲቲ፣ የማዕድን እና ታዳሽ ኃይል እንዲሁም የቱሪዝም እና አገልግሎት ዘርፍ ያላቸውን አማራጮች በዚህ ፎረም በስፋት ይተዋወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በፎረሙ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን በግል ባለሀብቱ እና በመንግስት መካከል የፖሊሲና የኢንቨስትመንት ውይይት ይደረጋል እንዲሁም የአቻ ለአቻ ቢዝነስ ውይይቶች ፤ኢንቨስትመንት አማራጭ ኤግዚቢሽኖች እና በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ጉብኝት እንደሚደረግ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡@seco


