“ኃላፊነታቸው ባልተወጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ ወስጃለሁ” የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

ቢሮው በ5ወራት ውስጥ በ179 ሰራተኞች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መወሰዱን ነው ያስታወቀው።

በቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዱራህማን በዕቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች እንዳሉ ተናግረዋል።

ከዋና መስራያ ቤት አንስቶ በሁሉም ቅርንጫፎች እና ወረዳዎች ጽህፈት ቤቶች ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ የስነ_ምግባር፣ በሰርቪላንስ ካሜራ በመታገዝ ክትትልና ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል።

በዚህም ሃላፊነታቸው በአግባቡ ተወጥተው ባልተገኙ 20 አመራሮችና 159 ፈፃሚዎች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል ።

የክትትልና ድጋፍ ስራው የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው በአገልግሎት አሰጣጥ ፣ በሀርሞናይዜሽን ፣ በቲን ቁጥር አሰጣጥ ፣ በኢፋይልና ኢፔመንት ፣ በመዝጊያ ኪሊራንስ እንዲሁም በመማክርት ጉባኤን ውይይት የተጠናከረ ስራዎችን በመስራት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የቢሮው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ በበኩላቸው የሚሰጡ አገልግሎቶችን የጥራት ደረጃ በማሳደግ ገቢን በፍትሃዊነት መሰብሰብ ይገባል ብለዋል ።

አያይዘውም የከተማዋን የትኩረት ነጥቦችን የጋራ እውቀት በማድረግ አገልግሎት ጠያቂው ካለምንም እንግልት አገልግሎት የሚያገኝበትን ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር በየደረጃው ያለ አመራር ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል።@seco

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories