የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል
የዘመን ባንክ ቺፍ ሪቴል ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ አስራት ታደሰ ለቅዳሜ ገበያ እንደገለጹት የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስትራቴጂ ነድፎ እየሰራ ይገኛል፡፡
የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠርና ተኪ ምርቶችን በማምረት በኢኮኖሚው ዘርፍ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ተቋማቶቹ አሰራራቸውን ዘመናዊ ማድረግና የምርት ጥራት ማስጠበቅ ሲችሉ የተቋቋሙበትን አላማ ማሳካት እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡
ባንኩም የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ሊሞላ የሚችል ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ባንኩ የአነስተኛና መለስተኛ ተቋማት ያላባቸውን ክፍተት በመለየት የአቅም ግንባታ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመው ለኢንተርፕራይዞቹ የሂሳብ አያያዝ፣የውጭ ገበያ ትስስርና ከባንኮች ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንደሚያስፈልጋቸው ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ባንኩ ከስልጠናው ጎን ለጎን የኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ ፍላጎትን ለመሙላት እንደሚሰራም አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡
ባንኩ ቀደም ሲል በኤክስፖርት ምርት ላይ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና የሰጠ ሲሆን በተያዘው በጀት አመት 150 ለሚደርሱ ተቋማት የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የተች ዩር ቪዥን ሀላፊ አቶ አሸናፊ ብርሀኑ ባንኮች የፋይናንስ አቅማቸው ከፍተኛ እንደሆ ጠቁመው ከብድር በዘለለ አቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ተቋማቶቹን ብቁና ተወዳዳረሪ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡seco


