የብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የባንኮች አመታዊ የብድር እድገት በ24 በመቶ ተገድቦ እንዲቀጥል ወሰነ።
ኮሚቴው ባለፈው መስከረም ባደረገው ስብሰባ የብድር እድገቱ ቀደም ሲል ከነበረው 18 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ እንዲል ወስኖ ነበር።
ሆኖም ማእከላዊ ባንኩ ካለፈው መስከረም ወዲህ የወለድ እድገት ገደብ ሙሉ ለሙሉ እንደሚያነሳ ተጠብቆ ነበር።
ትላንት ስብሰባውን ያደረገው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ እንዳስታወቀው የብድር እድገት ገደቡ እስከ ቀጣዩ መጋቢት ባለበት እንዲቆይ ወስኗል።
በተመሳሳይ ገበያ ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ መጠን ለመቀነስ እና ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ለማስቀጠል በማሰብ የባንኮች መጠባበቆያ መጠን ወደ 10 በመቶ ከፍ እንዲል ወስኗል።@seco


