እስራኤል በቃጣር ላይ ከንፈር መንከሷ ይነገራል።
በተለይ ሚጢጢዬዋ የባህረሰላጤ አገር አሸባሪ ታስጠልላለች እና ትረዳለች የሚል ክስ ከእስራኤል በኩል ይቀርብባታል።
በቀጠናው የአሜሪካ አጋር የምትደረገው ቃጣር በርግጥም እስራኤል ጠላት የምትላቸውን በማስጠለል ትታወቃለች።
በዚህም እስራኤል የቃጣር ነገር በቃኝ ከማለት አልፋ የሃማስ አመራር ለመግደል በሚል ወደ ዶሃ ሚሳኤል መተኮሷ አይዘነጋም።
ከቀናት በፊት እስራኤል ለሶማሌላንድ እውቅና መስጠቷን ተከይሎ እንደ በርካታ ያካባቢው አገራት ቃጣር የተቃውሞ መግለጫ አውጥታ ነበር።
ሆኖም ተቃውሞዋ በስራኤል እንደሌሎች አገራት በቸልታ የታለፈ አልሆነው።
የስራኤሉ የዲያስፖራ ሚኒስትር በሃይለ ቃል አገሪቱን ወርፈዋል።
ቃጣር አገር አይደለችም በማለት ጭምር ነው የተናገሩት።@seco


