ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት 20 ሺህ ብር ተሻግሮ የነበረው ሰሊጥ በኩንታል 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በየቀኑ በሚደረገው ጨረታ ላይ በተለየው አመላካች ዋጋ የሰሊጥ ምርት በኩንታል ለመጀመሪያ ጊዜ 21 ሺህ ብር ተሸጧል፡፡

ምንም እንኳን በዚህ የክረምት ወቅት የምርት ዋጋ ጭማሪ  ማሳየት የተለመደ ቢሆንም  የዘንድሮው ጭማሪ ግን እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ነው ባለሞያዎች የገለጹት፡፡

በዚህ መሰረት ትላንት ረዕቡ ነሐሴ 6 ቀን 2018 በነበረው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጨረታ ላይ  የወለጋ ሰሊጥ በኩንታል 17 ሺህ ብር ሲሸጥ በአለም ገበያ በጥራቱ በጣም ተፈላጊ የሆነው የሑመራ ጎንደር ሰሊጥ በኩንታል 21 ሺህ ብር ሊሸጥ ችሏል፡፡

በዚሁ በጀት አመት መስከረም ወር ላይ 19 ሺህ ብር ተሸጦ የነበረ ሲሆን  ባለፉት ወራት ደግሞ በአማካኝ 18 ሺህ ብር ሲሸጥ ቆይቶ አሁን ላይ  በኩንታል 21 ሺህ ብር ማውጣት ችሏል፡፡

አምና በዚህ ወቅት 17 ሺህ 500 ብር አካባቢ መሸጡ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ የተመዘገበው ዋጋ ከቀደመው ዓመት 20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ሐምሌ 22 ቀን 2016 ከተጀመረ በኋላ  የሑመራ ጎንደር ሰሊጥ በአማካነካኝ 14 ሺህ ብር አካባቢ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከቀዳሚ ወጪ ሸቀጦች አንደኛው የሆነው ሰሊጥ በጸጥታ ችግር ምክንያት በበቂ ሁኔታ ለገበያ እየቀረበ አይደለም ሲሉ ላኪዎች እና ባለሞያዎች ስጋታቸውን ይገልፃሉ፡፡

ቀደም ሲል በአፍሪካ በዘርፉ ኢትዮጵያ እና  ሱዳን  ቀዳሚ አምራች ላኪዎች የነበሩ ቢሆንም በተለይ ምርት እና ምርታማነታቸውን እያሳደጉ የመጡ አዳዲስ አምራች አገራት ለኢትዮጵያ ገበያ ከፍተኛ ስጋት እንደሆኑ  ነው በባለሞያዎቸች  የሚገለፀው፡፡

አሁን ላይ በቀጠናው ባለው የፀጥታ ሁኔታ የሰሊጥ ምርት  ላይ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ  እየታየ ነው የዘርፉ ባለሞያዎቸች ለኢቢቪ  የገለጹት፡፡seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories