ብር በ3 በመቶ ተዳከመ

ዛሬ በተካሄደው የበጀት አመቱ የመጀመሪያ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የዶላር ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንና ብር በዶላር ፊት የበለጠ መዳከሙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው የጨረታ ውጤት አሳይቷል።

ብሔራዊ ባንኩ ለጨረታው 125 ሚሊዮን ዶላር መመደቡ ይታወሳል። እንዲያም ሆኖ 28 ባንኮች 470.17 ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ነበር ፈወላጎት ያሳዩት። በዚህ መሰረት ፍላጎቱ ጨረታ በ276 በመቶ ያህል ከፍ ያለ መሆኑን ያሳያል።

ከፍተኛው የጨረታ ዋጋ 1 ዶላር 163.98 ብር ሲሆን፣ ከቀዳሚው ጨረታ ከፍተኛው ዋጋ ጋር ሲነጻጸር የ4.4 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

የተሳካ ጨረታ ያለው አማካይ ዋጋ 1 ዶላር 161.79 ብር ሆኗል። ይህም ከቀዳሚው ጨረታ አማካይ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር የ3 በመቶ ያህል ብርን ያዳከመ ነው። ጨረታው ለበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሲሆን ከቀደመው ጨረታ በ6 ሳምንት ውስጥ የተደረገ ነው።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories