በኢቢቪ ዘጋቢ
የጥሬ ብር ዋጋ ባለፉት ሁለት ቀናት በተከታታይ ለፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።
በዛሬው የአለም ገበያ አንድ ወቄት ብር 89 ዶላር በመሸጥ አዲስ ሪከርድ ነው ያስመዘገበው።
ባለፉት ሁለት ቀናት ለታየው የብር ዋጋ መናር በአሜሪካ ማእከላዊ ባንክ መሪ ላይ ምርመራ መጀመር በምክንያትነት ይጠቀሳል።
ሆኖም ገንዘብ ያላቸው የሚጨበጥ ሃብት ለመያዝ መምረጣቸው እንደ ወርቅ እና ብር ላሉ የከበሩ ብረቶች ዋጋ መናር በምክንያትነት ይጠቀሳል።
በተጠናቀቀው 2025 ብቻ ብር ዋጋው የ150 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በአመት ውስጥ ወርቅ ወደ 63 በመቶ ዋጋው አሻቅቧል።
ለብር ዋገ መናር እንደ ወርቅ ሁሉ የአለም ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ባለሃብቱን ቋሚ ንብረት እንዲመርጥ እንዳደረገው ቢጠቀስም።
ብረቱ በዘመኑ ቴክኖሎጂ ተፈላጊ መሆኑ ለዋጋ ጭማሪው ተደራቢ ምክንያት ተደርጎ እየተወሰደ ነው።
ብር ለኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ስራ እንዲሁም ከኤአይ ዴታ ማእከል ግልጋሎት ጋር ተፈላጊነቱ ጨምሯል።
ባለፉት ቀናት የብር ማእድን ላሳየው ከፍተኛ ጭማሪ በአለም ላይ ዋነኛ የብር አቅራቢ የሆነችው ቻይና ከአዲሱ የፈረንጆች አመት መግቢያ አንስቶ በማእድኑ ኤክስፖርት ላይ የጣለችው የክልከላ ማእቀብ ሌላኛው ወሳኝ ምክንያት ተደርጎ ተቆጥሯል።


