ኢትዮጵያ ከማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ነፃ መሆኗ በይፋ ተበሰረ

ኢትዮጵያ ከማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ነፃ መሆኗ በይፋ ተበሰረ

በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን መንግሥት ዛሬ በይፋ አስታውቋል።

 በዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና በሀገሪቱ የጤና መመሪያ መሠረት፣ ወረርሽኙ አከተመ የሚባለው የመጨረሻው ታካሚ ከታወቀበት ዕለት ጀምሮ ለ42 ተከታታይ ቀናት ምንም ዓይነት አዲስ ታካሚ አለመገኘቱ ሲረጋገጥ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም ባለፉት 42 ቀናት ምንም ዓይነት በበሽታው የተያዘ ሰው ባለመመዝገቡ ሀገሪቱ ከወረርሽኙ ነፃ መሆኗ ተረጋግጧል።

ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ሕዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከ3 ሺህ 800 በላይ ምርመራዎች የተከናወኑ ሲሆን፣ በበሽታው ከተያዙ 14 ዜጎች መካከል የዘጠኙ ሕይወት ሲያልፍ፣ አምስቱ አገግመው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የማብሰሪያ መድረክ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ኢትዮጵያ ከወረርሽኙ ነፃ መሆኗን አብስረዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፣ ምንም እንኳን የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት በወረርሽኙ ቢቀጠፍም፣ ከተባበረው የፈጣን ምላሽና አመራር ስኬት አንጻር ሀገሪቱን ከከፋ ችግር መታደግ መቻሉን ገልጸዋል።

በመድረኩ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ ይህም ስኬት የጤና ተቋማትና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ውጤት መሆኑ ተመላክቷል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories