በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ2018 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም መድረክ ላይ እንደገለጹት በዚህ ዓመት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ይሰጣል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ፈተናው በወረቀትና በበይነ መረብ ሲሰጥ እንደረበር ጠቁመው በዚህ ዓመት የሚሰጠውን ማጠናቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ለዚህም የተለያዩ ግብዓቶች ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን በፈተና ጣቢያዎች በቂ የኢንተርኔት አቅርቦት እንዲኖር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመነጋገር ይሰራል ብለዋል።
ክልሎች በዚህ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች እንዳይኖሩ በቂ ኮምፒዩተር ፣ ኔትዎርክና አማራጭ የሀይል አቅርቦት እንዲኖር ልዩ ትኩረት ሰጥተው መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበው ለተማሪዎች በቂ ሥልጠና መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የክልልና ከተማ መስተዳድሮች ይህንን አውቀው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።@SECO


