ድምጻዊ ግርማ ነጋሽ (ከ1936 እስከ 2019)

ምነው ተለየሺኝ ፣ የኔ ሀሳብ ፣ እንገናኛለን ፣ አልበቃኝም ገና እና በሌሎች  ዘፈኖቹ የሚታወቀው ድምጻዊ ግርማ ነጋሽ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡

ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ በ1936 ዓ.ም አዲስ አበባ ፊት በር በሚባለው ሠፈር የተወለደ ሲሆን በ83 አመቱ መስከረም 12 ቀን 2019 ምሽት ላይ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፡፡

ግርማ ነጋሽ ምነው ተለየሺኝ ፣ የኔ ሀሳብ ፣ እንገናኛለን ፣ አልበቃኝም ገና እና በሌሎች ተወዳጅ ዘፈኖቹ ይታወቃል፡፡

ድምጻዊ ግርማ ነጋሽ የሙዚቃን  ከአብሮ አደጉ ሰይፈ ዮሃንስና ከአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ጋር በመሆን የሙዚቃ ህይወቱን ሀሁ እንደጀመረ ይነገራል፡፡

 ከ1952 ዓ.ም ጀምሮ በፖሊስ ኦርኬስትራና በብሄራዊ ትያትር ቤት ለአጭር ጊዜ ሰርቷል።  

ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረክ ላይ ይዞ የቀረባቸው ዘፈኖች «የኔ ሃሣብ»ና «ምነው ተለየሽኝ» በመባል የሚታወቁትን ነው።

በሙዚቃው ብዙም ሳይገፋ በቤተሰብ ተጸዕኖ ሳቢያ ሙዚቃን ተሰናበተና በኮካኮላ ኩባንያ ውስጥ  የሽያጭ ሰራተኝነት፣ ከዛም በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ አገልግሏል።

ድምጻዊ  ግርማ ነጋሽ ከሚታወቅበት የሙዚቃ ስራወቹ በተጨማሪ በ በስፖርት እና የአርብ ምሽት የባህል ሙዚቃ አዘጋጅና አቅራቢም በመሆን  በጋዜጠኝነትም ሰርቷል፡፡

በ2015 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሞያወች ማህበር አስተባባሪነት በቨርጂኒያ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ጉዞ ላይ ላበረከተው አስተዋጾ የምስጋና ቀርቦለታል፡፡

ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ የ3 ወንዶችና የ1 ሴት ልጅ አባትም ነበር፡፡SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories