በትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ተቋቋመ

መንግስት በትግራይ ክልል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት ለመፍታት የተደረገው  ጥረት በሕወሐት ዕንቅፋትነት የተነሣ ሳይሳካ እንደቀረ አስታውቋል።

የሕወሐት አመራር ለአራተኛ ጊዜ የጀመረው አውዳሚ ጦርነት ለአራተኛ ጊዜ በሕወሐት ሽንፈት ተጠናቋል ሲል ገልጿል።

የትግራይ ሕዝብ በፌዴሬሽኑ ውስጥ የሚገባውን ቦታ አግኝቶ ሰላሙን ማስከበር፣ ትኩረቱን በልማት ላይ ማድረግና ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ጸንቶ መኖር አለበት ሲል መንግስት አስታውቋል።

እነዚህን ሁኔታዎች ለማመቻቸት እንዲቻል የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ መሠረት ተመስርቷል፡፡

ባለአደራ አስተዳደሩም ለሚቀጥሉት 6 ወራት ትግራይን የሚያስተዳድር ይሆናል።

ተግባሩንም ከፌዴራል መንግሥት በሚሰጠው አቅጣጫ እና መመሪያ መሠረት የሚያከናውን ሲሆን የባለአደራ አስተዳደሩ ዋና አስፈጻሚዎችም ሹመውለታል፡፡

በዚህም መሰረት

1. አቶ አሰፋ አብርሃ ሐጎስ የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ

2. ⁠ዶክተር ቴዎድሮስ አረጋይ ወ/ሥላሴ – የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ

3. ⁠ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ – የጸጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ

4. ⁠አቶ ረዳኢ ኃለፎም ወ/ሥላሴ – የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና አስፈጻሚ

5. ⁠ዶክተር ሽሻይ አማረ – የመቐለ ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories