የአዲስ አበባ ኅብረት ስራ ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የብድርና የቁጠባ ኅበረት ስራ ማኅበራት ለአባሎቻቸው የሚያቀርቡት ብድር ከሰባት ቢሊየን ብር መብለጡን ይፋ አደረገ፡፡
የዐለም አቀፉን የቁጠባና ብድር ኅበረት ስራ ቀን ለማክበር እየተዘጋጀ የሚገኘው ኮሚሽን እንዳስታወቀው የማኅበራቱ ዐመታዊ የብድር አቅርቦት 7.4 ቢሊየን ደርሷል፡፡
ይህ ብድር አባላት ለራሳቸው የስራ ዕድል እንዲፈጥሩና ከፍ ያለ ግብይት እንዲካሄድ አስችሏል፡፡
የኮሚሽኑ የፋይናንስ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አክሊሉ እንደገለጹት በርካታ ሰዎች ብድሩን ተሽከርካሪ ገዝተው በሜትር ታክሲ አገሎግሎት ላይ ለመሰማራት እየተጠቀሙበት ነው፡፡
ማኅራቱ ራሳቸውም በቅጥር ብዙ የስራ ዕድል ፈጥረዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኙት የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማኅበራት ከ1100 ይበልጣሉ፡፡
በተቋማቱ ውስጥ በመቀጠር አለዚያም ብድር በመውሰድ በየዐመቱ ቢያንስ አስር ሺህ ሰዎች ወደ ስራ እየተሰማሩ ነው፡፡
ኅብረተሱቡም ሆነ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት እንደሰጧቸው አቶ ተስፋዬ ይናገራሉ፡፡
ማኅበራቱ የቆጠቡት ገንዘብም ከሰባት ቢሊየን ብር በልጧል፡፡
ይሁንና ኮሚሽኑ ማኅበራቱን በአግባቡ ሊያስተናግድ በሚችልበት ልክ እንዳልተደራጀ ምክትል ኮሚሽነሩ አቶ ተጫነ አዱኛ አስታውቀዋል፡፡
በተለይያ በቂ ባለሙያ ባለመኖሩ አሰራራቸውን በአግባቡ እየተከታተሉ ለማረም ያስቸግራል፡፡
ማኅበራቱ አሰራራቸው ግልጽነት እንዲኖረው እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም ብድር ሲሰጡና ዕዳ ሲሰበስቡ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ ተጫነ አስታውቀዋል፡፡
ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግራቸውን ለመፍታት ለተሰባሰቡት አባሎቻቸው አሰራራቸውን ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸውም ነው ያሳሰቡት፡፡
ዓለም አቀፉ የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ቀን ነገ በከተማ ደረጃ በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል ይከበራል፡፡
ከኅዳር ወር ሶስተኛ ሳምንት ጀምሮ ደግሞ በክፍለ ከተማና በየወረዳው ክብረ በዐሉ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡
በዐለም ለ78ኛ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ35ኛ ጊዜ የሚቀበረው ቀን መሪ ሃሳብ የኅበረት ስራ ፋይናንስ ለተረጋጋ ኢኮኖሚ ልዩ ምልክት ነው የሚል ይሆናል፡፡SECO


