የጉምሩክ ኮሚሽን የባቡር ድርጅቱን ማሳሰቢያ ተከትሎ የአሰራር ለውጥ እንዲደረግ መመሪያ ሰጠ

በባቡር ወደ አገር ውስጥ የሚጓጓዙ ጭነቶች የጉምሩክ ስነ ስርአት በገላን ጣቢያ እንዲፈፀም የአዲስ አበባ ቅርንጫፍን አዟል

የጉምሩክ ኮሚሽን ትላንት ህዳር 2 ቀን ለ ለአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት  በፃፈው ደብዳቤ እንደገለፀው በባቡር ገላን ሁለገብ ወደብ የሚደርሱ ጭነቶች ለጉምሩክ ስነ ስርአት ወደ ቃሊቲ ጣቢያ በመኪና ተጭነው እየተጓጓዙ መሆኑን ጠቅሶ ይህ አሰራር እንዲቀር ነው ያሳሰበው።

ለቅርንጫፍ /ጽ/ቤቱ በተፃፈው እና ኢቲቢዝነስቪው የተመለከተው ቅጂ እንደሚያመለክተው የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ከቀናት በፊት ለጉምሩክ ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ እንደገለፀው  በቅርቡ በተደረገ ክትትል በባቡር ገላን ሁለገብ ወደብ የሚደርሱ ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት እንዲፈጸምላቸው በከባድ መኪና ተጭነው ወደ ቃሊቲ እየተጓጓዙ ነው ሲል ጠቅሷል።  አክሎም ሁኔታው የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ ከመጨመሩም በላይ የደንበኞችን እርካታ በመቀነስ ለቅሬታ መበራከት ምክንያት ሆኗል ነው ያለው።


“በተጨማሪም፣” አለ የባቡር ድርጅቱ “ለኮሚሽኑ በላከው ደብዳቤ አላስፈላጊ መዘግየትን እንዲሁም ተደጋጋሚ የማስጫኛና ማውረጃ ተጨማሪ ወጪን እንዲሁም የሎጂስቲክስ ሰንሰለቱን ማርዘምን የሚያስከትል ነው፣” ሲል ነው የገለፀው።

ይህ የተንዛዛ አሰራር የመንግሥትን የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ስትራቴጂ የሚቃረን በመሆኑ መዳረሻቸው ገላን ሁለገብ ወደብ (GMP) የሆኑ ሁሉም ኮንቴይነሮች በዚሁ ወደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓታቸው ተጠናቆ እንዲለቀቁ በደንበኞች በቀጥታ እንዲደርሱ  ሲል ነው ለኮሚሽኑ የመፍትሄ ሃሳቡን በማሳሰቢያ ደብዳቤው ያጋራው።


 ይህንን ተለትሎ ነው እንግዲህ ኮሚሽኑ የአሰራር ለውጥ ተግባራዊ እንዲደረግ እና የጉምሩክ ስነ ስርአት በገላን ጣቢያ እንዲጠናቀቅ ረቡዕ እለት በፃፈው ደብዳቤ ያስታወቀው።

በደብዳቤው በሰጠው መመሪያ እንደገለፀው የተጠቀሰውን አላስፈላጊ ጫና ለማስቀረት ሲባል በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት በባቡር ተጓጉዘው ገላን ሁለገብ ወደብ የሚደርሱ ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ለማስፈፀም በከባድ መኪና ተጭነው ወደ ቃሊቲ እየተጓጓዙና በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት መፈፀምና መልቀቂያ የሚሰጣቸው የኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር ዕቃዎች ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተሽከርካሪ ማጓጓዝ ሳያስፈልግ በገላን ተርሚናል በሚገኘው የጉምሩክ ጽ/ቤት ተገቢውን የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አጠናቀው ለነፃ ዝውውር እንዲለቀቁ ሲል አስታውቋል።


የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የጋራ ንብረት የሆነው የባቡር ድርጅቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ስራውን ከማዘመን እና ማሳለጥ በዘለል በምልልስ እና አማራጭ የወደብ መዳረሻ የመሆን አቅሙን በይበልጥ ማስጋቱ ይገል።


በተጨማሪም ከባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ በተጨማሪ 6 የመልቲሞዳል ከዋኞች ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ፈቃድ መሰጠቱን ተከትሎ ይህንኑ ስራ መስፋት እየሰራ መሆኑ ነው የሚጠቀሰው።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories