የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍን በእጅጉ ሊያስፋፋ የሚችል አዲስለውጥ ባለፉት ሁለት ቀናት ተከስቷል። የገላን ሁለገብ/ Multipurpose ወደብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ሁለት ወሳኝ የቁጥጥርተቋማት ፈቃድ ማግኘቱ ነው የተሰማው፡፡
ውሳኔውለመልቲሞዳል የጭነት ማጓጓዣ እንቅስቃሴዎችና የጉምሩክክሊራንስ አገልግሎት እንዲውል መንገድ ተከፍቷል ነውየተባለው። የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ማሪታይምባለሥልጣን የሰጡት የተለያዩ ፈቃዶች፣ የሀገሪቱን የሎጂስቲክስመሠረተ ልማት ለማስፋፋት፣ የጭነት ማጓጓዣ አማራጮችንለማብዛትና ውድድርን ለማሳደግ ከፍተኛ አቅም አላቸው ሲሉነው ውሳኔውን ተከትሎ የዘርፉ ተዋንያን ለ ETBusinessViewየተናገሩት።
እርምጃው በመልቲሞዳል የጭነት ማጓጓዣ ንግድ ውስጥየኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ማጓጓዣ አክሲዮን ማኅበር (EDR) ተሳትፎንም የበለጠ ሊያጠናክር ይችላል ነው የተባለው። ETBusinessView ትናንት ሀሙስ አመሻሽ እንደዘገበው፣የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በEDR ጥያቄ መሠረት የገላን ወደብየጉምሩክ ክሊራንስ መዳረሻ እንዲሆን ፈቅዷል። ዛሬ በተሰጠ የተለየ ደብዳቤ ደግሞ የኢትዮጵያ ማሪታይምባለሥልጣን ገላን ተርሚናል ለEDR እና ሌሎች ስድስት ፈቃድላገኙ የመልቲሞዳል ኦፕሬተሮች የጭነት መዳረሻ ሆኖእንዲያገለግል ፈቃድ ሰጥቷል።
በሎጂስቲክስ አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ በሆኑት ሙሉፀጋ ንጋቱ የተፈረመው ደብዳቤ፣ EDR ገላን ተርሚናልንየመልቲሞዳል ጭነት መዳረሻ እንዲሆን ፈቃድ እንዲሰጠውለሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም. በጻፈውደብዳቤ መሠረት ጥያቄው መቅረቡን ያስታውሳል። ደብዳቤው፣ “በዚሁ መሠረት ተርሚናሉ በሚኒስቴሩ ጽሕፈት ቤትበመስክ ምልከታና ክትትል ተመርምሮና ተገምግሞ፣በመልቲሞዳል የማጓጓዣ ሥርዓት የሚጓጓዙ ኮንቴይነር ጭነቶችንለማስተናገድ መሠረታዊ መስፈርቶችን ያሟላ መሆኑተረጋግጧል” ይላል።
አክሎም፣ “ስለሆነም የሀገሪቱን የሎጂስቲክስ አፈጻጸምበሚያሻሽል መልኩ ተርሚናሉ ለመልቲሞዳል ኦፕሬተሮች መዳረሻሆኖ እንዲያገለግል ፈቃድ መሰጠቱን እናሳውቃለን” ብሏል። ሁለቱ ፈቃዶች የገላን ሁለገብ ወደብን በሀገሪቱ የሎጂስቲክስመረብ ውስጥ ያለውን ሚና በእጅጉ ሊያሳድጉ ይችላሉ ሲሉ ነው የሎጅስቲክ ባለሞያዎች ለዘጋቢያችን የገለጹት።
የመልቲሞዳል ኦፕሬተሮች ኮንቴይነር ጭነቶችን ወደ ተርሚናሉአጓጉዘው በዚያው የጉምሩክ ክሊራንስ እንዲያከናውኑ ማስቻሉ፣በነባር የሎጂስቲክስ መዳረሻዎች ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስያግዛል ሲሉም አክለዋል።
ለEDR ይህ እርምጃ ልዩ ጠቀሜታ አለው ያሉት የባቡር ድርጅቱምንጮች። ኩባንያው ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት የመልቲሞዳልማጓጓዣ ፈቃድ ቢያገኝም፣ እስካሁን በዘርፉ ያለው ተሳትፎ አነስተኛ ነበር። ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ለመንግሥታዊው ግዙፍ የሎጅስቲክስ ድርጅት የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖረት እና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) ብቻ የተያዘውን የመልቲሞዳል ማጓጓዣ ንግድ ለሌሎችተወዳዳሪዎች በመክፈት ላይ ትገኛለች።
በዚህም ከኢባትሎ በተጨማሪ ስድስት አዳዲስ ኦፕሬተሮችበዘርፉ ለመሳተፍ ፈቃድ አግኝተዋል። የገላን ተርሚናል ለእነዚህኦፕሬተሮች መዳረሻ እንዲሆን መፈቀዱም የጭነት ማጓጓዣአማራጮችን የበለጠ ሊያሰፋ ይችላል ነው የተባለው። የEDR በሎጂስቲክስ ዘርፍ የሚኖረው ተሳትፎ መጠናከር የኢትዮጵያና የጅቡቲ የባቡር ግንኙነት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታንም የሚጨምር እንደሆነ ነው እየተነገረ ያለው።
በተለይም ባለፈው ዓመት አጋማሽ በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ የተከሰተው የመርከብ ማጓጓዣ መስተጓጎል ከክልሉ የሚመጡ የነዳጅ አቅርቦቶችን በማስተጓጎሉ፣ ኢትዮጵያ በውጭ አቅርቦቶች ላይ ያላትን ጥገኝነትና አማራጭ የማጓጓዣ መስመሮች አስፈላጊነት አጉልቶ አሳይቷል ለዚህም የባቡር ሚና የሚታስ ነው ሲሉ ነው የዘርፉ ከዋኞች የገለፁት።SECO


