ዳሸን ባንክ ከታዋቂው ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ ጋር በመተባበር የክላሲካል ሙዚቃ የብራንድ መለያ በሸራተን አዲስ አስመርቆ ይፋ አድርጓል።
ሙዚቃው በሁሉም የባንኩ የአገልግሎት መስጫ አውታሮች ለደንበኞች ልዩ፣ ወጥ እና የማይረሳ ተሞክሮ ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆነው ኢትዮጵያዊው የኮንሰርት ፒያኒስት እና የሙዚቃ ደራሲ ግርማ ይፍራሸዋ ጋር በመተባበር የተሰራው አዲስ የድምፅ መለያ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ እርምጃ እንደሆነ ተነግሯል።
በዳሸን ባንክ የደንበኞች መገልገያ ማዕከላት ጥበብን፣ ውበትን እና ስሜታዊ ትስስርን በማስረጽ የደንበኞችን ተሞክሮ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ታስቦ መሰራቱ ተገልጿል።
ደንበኞች ከባንኩ ጋር በሚገናኙበት በማንኛርዑም ቦታ የዳሸን ባንክን የክላሲካል ሙዚቃ የብራንድ መለያ የሚደመጥ ሲሆን በባንኩ ቅርንጫፎች፣ በጥሪ ማዕከል፣ በኤቲኤም (ATM) ማሽኖች እና በሌሎች የደንበኞች መገኛ ቦታዎች እንደሚቀርብ ባንኩ አስታውቋል።
የሙዚቃው መዘጋጀት ባንኩ ከደንበኞች የሚያገኘው እምነት ደረጃውን ይበልጥ ከፍ እንዲያደርግ፣ አዳዲስ ሀሳቦችን እንዲቀበል እና የላቀ አገልግሎት እንዲሰጥ መነሳሳትን ይፈጥርላታል፡፡
የመለያ ሙዚቃው ብቻ ሳይሆን ምንጊዜም የባንኩ ዕድገና ስኬት ዋነኛ አካል ለሆኑት ደንበኞች የቀረበ የምስጋና መግለጫም ጭምር እንደሆነ ባንኩ ጨምሮ ገልጿል።
የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ እንደገለጹት እንድ ብራንድ የሚነሳው በአርማው፣ በቀለማቱ ወይም በማስታወቂያዎቹ ብቻ ሳይሆን በሚፈጥረው ስሜት፣ በሚያሳድረው ትዝታ እና በሚያስተላልፋቸው እሴቶች ጨምር ነው።
ይፋ የተደረገውክላሲካል ሙዚቃ ከሙዚቃ መለያ በላይ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው የዳሸን ባንክን ማንነት የሚገለጽበት ልዩ ትዝታዎችን የሚፈጠርበት እና ለባንኩ ብራንድ ዘላቂ የሙዚቃ አሻራ የሚኖርበት አዲስ የጥበብ ቋንቋ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።
ባንኩ “በኢኮስ ኦፍ ዳሽን” አማካኝነት የኢትዮጵያን እምቅ የሙዚቃ ባህል እያስተዋወቀ ከደንበኞቹ ጋር ጥልቅ ስሜታዊ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ልዩ ተሞክሮ ፈጥሯልብለዋል።
ዳሸን ባንክ ተቋማዊ ራዕይን ከዓለም አቀፍ ደረጃ የጥበብ ብቃት ጋር በማጣመር፣ የባሀል ጥበቃንና የፈጠራ ዕድገትን ለመጪው ትውልድ እየደገፈ በአገልግሎች ልቀት አዲስ መለኪያ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ ለኢቲ ቢዝነስ ቪው እንደገለፀው በሙዚቃ መሳሪያ የተቀነባበረው አልበም አስር ሙዚቃዎችን የያዘ ነው።
ባንኩ በሙዚቃው ዘርፍ ተባብሮበመስራት ትልቅ አሻራ እንደጣለ ተናግሯል።
በአልበሙ የተካተቱት ሙዚቃዎች ባንኩን ከማህበረሰቡ ጋር የሚያስተሳስሩና ተፈጥሮነና አብሮነትን የሚያሳዩ እንደሆኑ ገልጿል።
ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ከሆኑ የግል ንግድ ባንኮች አንዱ ሲሆን ፈጠራ የታከለባቸውን የፋይናንስ አገልግሎቶችንና መፍትሄዎችን፣ የላቀ የደንበኞች አገልግሎትን እና ትርጉም ያለው ማህበራዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር ቁርጠኛ ሆኖ በመስራት ላይ ያለ ባንክ ነው።SECO


