የማይበገር ንግድና ዘላቂ የእሴት ሰንሰለት በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ እንደገለጹት መንግሥት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙን ተግባራዊ በማድረግ ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው።
በተፈጠረው የወጪ ንግድ እድል በ2018/2019 የበጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ 11.2 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
ከወጪ ንግድ ከተገኘው ገቢ ከጥራጥሬና ቅባት እህሎች 572 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ይኸውም ከጠቅላላውን የወጪ ንግድ ገቢ 5 በመቶ ብቻ ድርሻ እንዳለው ጠቁመዋል።
በዘርፉ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ምርትን ማሳደግ፣እሴት መጨመር፣ የገበያ ተሳትፎና ተደራሽነትን ማስፋት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ጥራጥሬና ቅባት እህሎች ላኪዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ኢዳኦ አብዲ በበኩላቸው ሀገሪቱ ጥራጥሬና ቅባት እህሎች ምቹ ስነ ምህዳር እንዳላት ጠቁመው በዘርፉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ምርትን ማሳደግ ይጠበቃል ብለዋል።
በአለም ገበያ ተፎካካሪና ተፈላጎ ለመሆን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች የምርት ጥራት ማስጠበቅ ላይ መስራት እንዳለባቸው አንስተዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ተሳትፎዋን ለማሳደግና ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ለመቀላቀል እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ የማህበሩ አባላት የገዢ አገራትን ሕግና የጥራት መስፈርቶች አውቆ መተግበር እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።SECO


