ጀነራል አል ቡርሀን የሚመሩት የሱዳን ጦር የኢትዮጵያ የአደራዳሪነት ጥያቄን በይፋ ውድቅ አድርጎታል።
ጀነራል ዳጋሎ የሚመሩት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር በአንፃሩ የኢትዮጵያን የድርድር ጥሪ እንደሚቀበለው አሳውቋል።
የቡርሀን ሃይል ኢትዮጵያ ለአንድ ወገን ታደላለች፣ የፈጥኖ ደራሽ ጦሩ ድሮኖች ከድንበሯ እንዲነሱ ፈቅዳለች፣ አደራዳሪነት ሳይሆን የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነት በገለልተኛ ወገን ሊጣራ የሚገባው ነው ብሏል።
የሱዳን ሲቪል ሃይሎች ህብረት የሚባል ቡድን ደግሞ የኢትዮጵያን ወንድማዊነት በመጥቀስ ድርድሩን ተቀብሏል።
የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት አራት አመታት ያስቆጠረ ሲሆን ሺዎችን ለሞት፣ ሚሊየኖችን ለስደትና ለቀውስ ዳርጓል።
አዲሱ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የአደራዳሪነት ጥሪ የተለያዩ ምላሾችን ማስተናገዳቸው የኢትዮጵያ እና ሱዳን ጉዳይ ብዙ ውዝግቦች ያሉበት መሆኑን ያመላክታል።seco

