በአንድ አመት ውስጥ በጂታል ክፍያ ስርአት 18ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ዝውውር መፈጸሙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

በኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ኮንፈረንስ 2.0.  ላይ ለአምስት አመት የሚቆይ (2026-30) የብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ በብሔራዊ ባንክ ይፋ ሆኗል።

የመጀመሪያው የ2021-24 ብሄራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ  ላይ ህግ ማውጣት፣ተቋማት አገልግሎቱን እንዲሰጡ ማስቻልና ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም መሠረተ ልማት ዝርጋታ መከናወናቸው ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርአት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ዳምጠው ለቅዳሜ ገበያ እንደገለጹት በኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ትልቁ ሚና የገንዘብ ዝውውር ፈጣን ቀልጣፋ ወጪ ቆጣቢ መሆን አለበት።

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል የክፍያ ስርአት ጉልህ ሚና ይጫወታል።

ባለፈው አንድ አመት በዲጂታል ክፍያ ስርአት 18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር መዘዋወሩን አስታውቀዋል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚው  የሚንቀሳቀሰው በጥሬ ብር ነው ያሉት አቶ ሰለሞን ይህን መለወጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በቀጣይ አምስት አመት 75 በመቶ  ክፍያ ስርዓት በዲጂታል እንዲያልፍ፣ አሁን ላይ በወንዶችና በሴቶችን የዲጂታል ክፍያ ስርአት አጠቃቀም 24 በመቶ ልዩነት ሲኖረው  በቀጣይ አምስት አመት የሴቶችን ተጠቃሚ ቁጥር በማሳደግ ልዩነቱን  ወደ  3 በመቶ ለማውረድ ይሰራል ብለዋል።

ያለፈውን አምስት አመት ግምገማን ውጤት መሰረት በማድረግ በቀጣይ  አምስት አመት ኢትዮጵያውያን የሚያገናኝ የታመነ፣ የተቀናጀ እና ተደራሽ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ስነ-ምህዳር እውን ለማድረግ  ትኩረት እንደሚሰጥ ተገልጿል።@Seco   

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories