14 አገራት የሚሳተፉበት ግዙፍ የእንስሳት ልማት ኤክስፖ አዲስ አበባ ላይ ሊካሄድ ነው

ኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የከብት እርባታ ዘርፏን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ ያለመ ዋና ዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ልታስተናግድ ነው።

ይህ 14ኛው የኢትዮ የዶሮ እርባታ ኤክስፖ ፣ 10ኛው የአፍሪካ የእንስሳት እርባታ ኤግዚቢሽንና ኮንግረስ ከሌሎች ተጓዳኝ ዝግጅቶች ከመጪዉ ከጥቅምት 20 ቀን ጀምሮ ለ 3 ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በፕራና ኢቨንትስ የተዘጋጀው ይህ ሁሉን አቀፍ የንግድ ትርዒት፣ ለበርካታ ተከታታይ ዓመታት ከሚሳተፈው የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ፓቪሊዮን ጨምሮ ከ14 አገሮች የተውጣጡ ከ80 በላይ ዓለም አቀፍ ተሳታፊዎችን ያስተናግዳል ተብሏል።

የዝግጅቱ ዋና ዓላማ የዶሮ እርባታ፣ የወተት፣ የሥጋ፣ የንብ እና የዓሣ ሀብት ዘርፎችን ምርታማነት በማሳደግ ብሔራዊ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

ዝግጅቱ ከቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ብራዚል፣ ኔዘርላንድስ እና ቱርክን ጨምሮ ከ14 አገሮች የመጡ ተሳታፊዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ከ5,000 በላይ ጎብኚዎች እንደሚኖሩት ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የወተት ምርትን ወደ 11.7 ቢሊዮን ሊትር እና የእንቁላል ምርትን ወደ 9.1 ቢሊዮን ለማሳደግ የያዘውን የአራት ዓመት ዋና ዕቅድ (Master Plan) እውን ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories