ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ቀዳሚው የሆነው ዘምዘም ባንክ አክሲዮን ማኅበር፣ ታኅሣሥ 05/2018 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የላቀ አፈጻጸሙን አስታውቋል።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ናስር ዲኖ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከ1 ነጥብ 23 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማስመዝገብ ለባለአክሲዮኖቹ የትርፍ ክፍፍል ማዳረስ ወደሚጀምርበት ምዕራፍ ተሸጋግሯል።
ባንኩ ከዚህ ስኬት በተጨማሪ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የ5 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል መስፈርት በወቅቱ ማሟላት ችሏል።
ዘምዘም ባንክ ዲያስፖራውን በባንኩ እንዲገለገል በማድረግ 64 ነጥብ 7 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን፣ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ አጠቃላይ ሃብቱ ከ16 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል።
ከ18 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ባንኩ የተቀማጭ ገንዘቡ መጠን 11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር መድረሱን ቅዳሜ ገበያ ሰምታለች።Seco


