አቶ ፍትህአወቅ የወንድወሰን የምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ (EAES) ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የኢትዮጵያ አርታዒያን ማህበር እንዳስታወቀው ማህበሩን በሊቀመንበርነት የሚመሩት አቶ ፍትህአወቅ የወንድወሰን የምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ (EAES) ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2026 በናይሮቢ በአፍሪካ ሚዲያ ፌስቲቫል ማጠናቀቂያ ላይ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ የአመራር ምርጫ ላይ አቶ ፍትህአወቅ የወንድወሰን በፕሬዝዳንትነት ወ/ሮ ዙቤይዳ ካኑ (ከኬንያ አርታዒያን ማህበር ) በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተመርጠዋል፡፡

የአቶ ፍትህአወቅ  በፕሬዝዳንትነት መመረጥ የኢትዮጵያ አርታዒያን ማህበር በቀጠናው ላይ ያለውን ተሰሚነት የሚያጎላ ሲሆን ፤ በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ማህበራችን የቀጠናውን የሚዲያ ገጽታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ድንበር ተሻጋሪ የአርታኢያን ትብብሮችን ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት ለመግለፅ ይወዳል ሲል ማህበሩ አስታውቋል።

የምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ (EAES) በኬንያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ዩጋንዳ ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ የሚገኙ የአርታዒያን ማኅበራት ጥምረት ነው፡፡

አቶ ፍትህአወቅ የወንድወሰን የቅዳሜ ገበያ ባልደረባ  እንደሆኑ ይታወቃል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories