የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት ከአሜሪካ ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት፣ ወደ አገራቸው መመለስ የማይችሉ የሶስተኛ ወገን ስደተኞችን በጊዜያዊነት ለመቀበል መስማማቱን ይፋ አደረገ።
በኪንሻሳ የሚገኘው የኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ሚኒስቴር ሚያዝያ 5 ቀን 2026 (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር) ባወጣው መግለጫ፣ ይህ ጊዜያዊ አቀባበል በዚህ ወር ውስጥ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምርና በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ውስጥ የተመረጡ ስፍራዎች ስደተኞቹን ለማስተናገድ መዘጋጀታቸውን አስታውቋል።
ይህ እርምጃ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ስደተኞችን ወደ ሶስተኛ አገራት በማዛወር የሚከተለውን አዲስ የዲፖርቴሽን ስትራቴጂ አካል ሲሆን፣ ኮንጎም ከዩጋንዳ በመቀጠል ይህንን ስምምነት የተቀበለች ቀጣይ የአፍሪካ አገር ሆናለች።
መንግስት ባወጣው መግለጫ፣ ይህ አሰራር የአገሪቱን ሉዓላዊነት በጠበቀ መልኩ እና ለስደተኞች መብት ካላት ዓለም አቀፋዊ ቁርጠኝነት በመነጨ የሚከናወን መሆኑን ገልጿል። ስምምነቱ ስደተኞቹን በቋሚነት የማስፈር አላማ እንደሌለውና እያንዳንዱ ስደተኛ በኮንጎ ህግ መሰረት በግል እንደሚገመገም ተመልክቷል።@SECO


