ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ኩባንያዎቹ ምን እየሰሩ ነው?

የብረት ፋብሪካው በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ከአካባቢ ብከላ ነጻ የሆነ የምርት ሂደት መጀመሩ ተነግሯል፡፡

በሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኙት ስቲሊ አር ኤም አይ እና አስመን ኃ/የተ/ግ/ማ እንደ አገር በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተቀመጠውን የኢንደስትሪ ቅጥር ግቢ ሁለት በመቶ ከባቢ በአረንገዴ የመሸፈን ሃላፊነት ተወጥተው ኢንደስትሪዎቹ በሚገኙበት አቅራቢያ የማህበረሰብ አቀፍ የአካባቢ ልማት ላይ በጉልህ መሳተፍ እንደቀጠሉ ተገለጠ፡፡

ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ኢንደስትሪዎቹ በሚገኙበት የቢሾፍቱ ከተማ ቅጥር ግቢ እና አካባቢው በሚገኙ የተራቆቱ ስፍራዎቸን በአረንጓዴ የመሸፈን ስራ አጠናክረው የቀጠለ መሆኑ ታውቋል፡፡

በዚህም ዘንድሮው የክረምት ወቅት ከመንግስት ተረክበው መልሶ እንዲያገግም እየተንከባከቡት በሚገኘው ዲባዬ ተራራ በተከታታይ ለ 5ኛ አመት የተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡

ሀሙስ ሐምሌ 30 ቀን በተከናወነው እና የሁለቱ ኩባንያ ሰራተኞች በተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቢሾፍቱ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፅ/ቤት ኃላፊ ጣይቱ ያሚ የሁለቱ ድርጅቶች የአረንጓዴ ልማት ተግባር በአካባቢው ለሚገኙ በርካታ ኢንደስትሪዎች አርአያ እና ቀዳሚ ነው ብለዋል፡፡

እንደ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከኢንደስትሪ ግቢ 2 በመቶ በአረንጓዴ መሸፈን አለበት የሚለውን ህግ በተገቢው ሁለቱም ድርጅቶች መወጣታቸውን አስታውሰው፡፡

በተጨማሪነት በሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኙት ስቲሊ አር ኤም አይ እና አስመን ከኢንደስትሪ ስፍራዎቻቸው ባለፈ በአዋሳኝ የመንገድ አካባቢዎች እንዲሁም የተራቆቱ ቦታዎችን ወደ ጫካ የመለወጥ ስራን እንዲወጡ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጣቸውን ቦታዎች በዛፍ የመሸፈን ስራ ለአመታት በከፍተኛ ሃላፊነት ሲሰሩ እንደቆዩ ነው የተናገሩት፡፡

ከተማ አሰስተዳደሩ በአረንጓዴ ልማት ሆነ ሌሎች ማህበራዊ ሃላፊነት ስራዎች ጥሪ ባደረገ ጊዜ ቀድመው የሚገኙ መሆናቸውን ያስታወሱት የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ጣይቱ ይህን መልካም ተግባር ሌሎች በተሞክሮ እንዲወስዱት ነው ያሳሰቡት፡፡

በተከላው ወቅት የግዙፉ ብረት አምራች ስቲሊ አር ኤም አይ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ሰለሞን ደስታ እንደገለፁት ድርጅታቸው ስቲሊ በመርህ ደረጃ የተያዘውን የማህበራዊ ሃላፊነት የመወጣት ተግባር በህብረተሰብ ድጋፍ ላይ ብቻ ያተኮረ አለመሆኑን አስታውሰው፡፡

በአካባቢ ጠበቃ የሚሰራው ስራ የኩባንያው አይነተኛ መርህ መሆኑን እንደ ተጨማሪ የማህበራዊ ሃላፊነት ስራ ተግባር ለአብነት አንስተዋል፡፡

በዚህም ስቲሊ አር ኤም አይ ማምረት ከጀመረበት ያለፉት ሁለት አስርት አመታት ወደ ስራ ካስገባቸው እንደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት እንዲሁም የውሃ አቅርቦት አይነት ጉልህ ማህበራዊ ሃላፊነት ባልተናነሰ በአረንጓዴ ልማት ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

በግቢያችን በመንግስት ከተቀመጠው የሁለት በመቶ አረንጓዴ ሽፋን አልፈናል ያሉት ኢ/ር ሰለሞን ለምግብነት የሚያገለግሉ ዛፎችን የመትከል ግቡም ውጤታማ እየሆነልን ነው ሲሉ ነው ያከሉት።

ዋና ስራ አስኪያጁ በተጨማሪነት በአካበቢው በሚገኙ ተራራማ ቦታዎች ችግኝ በመትከል እና በቋሚነት ባለሞያ ቀጥሮ በመንከባከብ ከፍተኛ ውጤት ማስገኘት መቻሉንም እንደ ከፍተኛ ተጠቃሽ ውጤት አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም ኩባያው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በማድረግ ዘመናዊ የምርት ሂደትን  ያስተዋወቀ መሆኑን ጠቅሰው። ይህም የአካባቢ ጥበቃ አካል ነው ሲሉ በአገር ደረጃ በዘመናዊነት ቀዳሚ የሆነው የብረት ፋብሪካ የስራ ሂደት ጠቅሰዋል፡፡

በተመሳሳይ ከፍተኛ ተኪ የብረት ምርት እና የግንባታ ግብአቶችን በማምረት ላለፉት ሩብ ክፍለ ዘመናት መቆየት የቻለው የአስመን ስራ አስኪያጅ አቶ ኑሩ እሸቱ የአረንጓዴ አሻራ ስራ የኩባንያቸው ባህል መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጠል መሆኑን ነው የገለፁት፡፡

እንደ አስመን ስራ አስኪያጅ ገለፃ የኩባንያውን ሰራተኛና የአካበባቢውን ነዋሪ  በማሳተፍ ሲከናወን የቆየው የአካባቢ ጥበቃ ስራ በተለይ አሁን በፋብሪካዎቹ እና የችግኝ ተከላ በሚከናወንበት አቅራቢያ በሚገኘው በአቡሴራ እየተገነባ የሚገኘው የቢሾፍቱ አየር መንገድ ምቹ እና አረንጓዴ ከባቢ በመፍጠር የራሱ ሚና አለው ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

የሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቦርድ ተወካይ አቶ ግርማ አዲስ በበኩላቸው ስቲሊ አር ኤም አይ እና አስመን አረጋውያን የማገዝ፣ ተንከባካቢ የሌላቸው ህጻናትን ከጎናቸው በመሆን አሌንታነት በማረጋገጥ፣ የምገባ ማዕከላትን በማቋቋም፣ በተለያየ ምክንያት እና እንደ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ አይነት አጣዳፊ ሁኔታ ሲያጋጥም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ የወገን ደራሽ የመሆን ሚናቸውን ከምስረታቸው ጀምሮ እንደተገበሩ ገልፀዋል፡፡

ይህንኑ ተግባር ወደ ፊትም በተቀናጀ መልኩ እንደ ግሩፕ ለማከናወን ፋውንዴሽን መቋቋሙን ነው አክለው የገለጹት፡፡

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories