በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች ሴት በታክስ ተመላሽ በጠየቀችው ከፍተኛነት ተጠርጥራ ምርመራ ይደረግባታል ያንንም ተከትሎ የአገሪቱ የታክስ ገቢ ተቋም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱ ነው የተገለፀው፡፡

ሆኖም ተከሳሽ በ750 ሺ ዶላር ታክስ ምላሽ ጥያቄ እና ተያያዥ ሂደት እንዴት እንዲ አረግሽ ተብላ ስትጠየቅ ወደ ኢትዮጵያ ስትመላለስ እንደነበር አስታውሳ በአፍሪካዋ አገር ያለው የኢንተርኔት ደካማነት ለችግሩ አይነተኛ ምክንያት እና ሰበብ እንደሆነባት በመናገር ከክሷ ለጻ ለመውጣት ሞክራ ነበር፡፡

ነገር ግን የሀገር ውስጥ ገቢዎች መሥሪያ ቤትም ሆነ በሀሰተኛ ጥያቄዋ ምክንያት የቅጣት ውሳኔ ያሳለፉባት ዳኛ ሰበቧን አላመኑም።

በወጡ ዘገባዎች መሰረት ሄለንየ750 ሺ ዶላር ጥያቄውን ከማቅረቧ በፊት በድርጅቷ የኦንላይን የገቢዎች መለያ ላይ ቢያንስ 60 ጥቃቅን ማስተካከያዎችን አድርጋ ነበር ተብሏል። ሆኖም የታክስ መስሪያ ቤቱ የተመላሽ ጥያቄው ከመቅረቡ በፊት የነበራትን የድረገጽ ላይ እንቅስቃሴ ሲከታተል እንደቆየ ነው የታወቀው፡፡ ይህም ክትትለ ሴቲቱ የእዳ እና እሬዲት ማስተካከያዋን እና የግል ንብረቶቿን ስትለውጥ እንዲሁም የቀጥታ የግብር ክፍያ መከታተያ መሰረተ ልማቱን ስታጠፋ እና ስታበራ እንደነበር ነው በክትትሉ መታዘብ የተቻለው፡፡

ዘገባዎች እንደ ገለጹት ትላነት ሀሙስ ሄለን በቀረበችበት ፍርድ ቤት በተካሄደው የቅጣት ውሳኔ ላይ ዳኛው የኮምፒተር ክትትሉ የሴትዮዋን ጥፋት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል ነው የተባለው፡፡

ሄለን እኤአ በ 2016 እ.ኤ.አ ራሷን ብቸኛ ዳይሬክተር እና ባለአክሲዮን በማድረግ Only1 Company Limited የተባለ ኩባንያ አቋቁማለች። ኩባንያው እንደ የጥሪ ማዕከል እና የፕላስተር ሥራ ንግድ ተመዝግቦ ነበር። ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2017 መጀመሪያ ድረስ፣ ባለድርጅቷ በኩባንያው ስም ሰባት የሀሰት የታክስ ሪፖርቶችን አቅርባለች። በአጠቃላይ ወደ 860 ሺ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ የጠየቀች ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ገቢዎችም ከ111 ሺ ዶላር በላይ በሂሳቧ ገቢ አድርጎላት እንደነበር ነው የታወቀው፡፡

ሆኖም በመጋቢት 2017 የመጨረሻው የ750,000 ዶላር የታክስ ተመላሽ ጥያቄ ሲቀርብ የገቢዎች ስርዓት ውስጥ ጥርጣሬ ስለፈጠረ፣ ጥያቄው “እንደሚታገድ” የሚገልጽ ደብዳቤ ለሄለን ይላክላታል፡፡

የመሥሪያ ቤቱ የኮምፒውተር ክትትል ሄለን ደብዳቤውን ከፍታ ማንበቧን እንዳሳየ የተነገረው፡፡

በሚቀጥለው ወር ጥያቄውን ለማስተካከል በርካታ “ያልተሳኩ” ሙከራዎችን ያደረገች ሲሆን፣ በአንድ መልእክቷ ለመጠየቅ አስባ የነበረው 75,000 ዶላር መሆኑን ለመሥሪያ ቤቱ ገልጻለች። የ750,000 ዶላር ጥያቄው በስህተት የተፈጠረ መሆኑን እና በኢትዮጵያ በነበረችበት ወቅት በነበረው መጥፎ የኢንተርኔት ግንኙነት ምክንያት ሳታስበው ተጨማሪ ቁጥር መግባቱን ተናግራለች ነው ያሉት የኒውዚላንድ ሚዲያዎች የፍርድ ቤቱን ውሎ ተከታትለው ባወጡት ዘገባ።

የሀገር ውስጥ ገቢዎች በኩባንያዋ ላይ ኦዲት ማድረግ ሲጀምር፣ ወደ ኢትዮጵያ ብዙ ጊዜ እንደተጓዘች እና የመጨረሻው ጥያቄ ስህተት እንደነበር በድጋሚ አረጋግጣለች ሲሉ አክለዋል።

ሴትየዋ ቤንዚን፣ ምግብ፣ አልኮል፣ ሲጋራ፣ ከረሜላ እና የክፍያ ቲቪ (ስካይ ቲቪን) ጨምሮ የተለያዩ ወጪዎችን የሚያሳዩ ደረሰኞችን ለኦዲተሮቹ እንደሰጠች ነው የተገለጸው። ሆኖም አብዛኞቹ የወጪ ማስረጃዎች ለግል ኑሮ የወጡ መሆኑ ነው የተገለጠው፡፡


ሴቲቱ ከታክስ ክፍያ ለማምለጥ ነው የተለያየ ሰበብ የምታቀርበው ሲል የገለጠው ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ሰበብም “በግልጽ የሀሰት” ነው ሲል አክሏል፡፡

ጉዳዩን የተከታተሉት ዳኛ እንዳሉት ጉዳዩ በመጨረሻ ላይ የተሳሳተ ቁጥር የመጨመር ቀላል ስህተት አልነበረም፤ ይልቁንም የሄለን የሀሰት ታክስ ሪፖርቶችን የማቅረብ ቋሚ አባዜ እንጂ፣ ማለታቸው ነው የተገለጸው፡፡

በመሆኑም የ60 አመት እድሜ ባለፀጋዋ ሄለን በ 10 ወራት የቤት ውስጥ እስር፣ የ150 ሰአታት የማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም የ15,000 ዶላር የካሳ ክፍያ (ለሀገር ውስጥ ገቢዎች በአምስት አመታት ውስጥ በየሳምንቱ እየከፈለች እንድታጠናቅቅ) ተፈርዶባታል።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories