ኢትዮጵያ አዲስ የግምጃ ቤት ሰነዶች እና ቦንድ መመሪያ ልታወጣ ነው

ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ሳምንታት የግምጃ ቤት ሰነዶች (ቲ-ቢል) እና የመንግሥት ቦንዶችን አሰጣጥ የሚገዛ አዲስ መመሪያ ልታወጣ እንደሆነ ተገለጸ። እርምጃው ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት ይሰጥ የነበረውን ቀጥታ ብድር ማቆሙን ተከትሎ፣ የበጀት ጉድለትን በሀገር ውስጥ የፋይናንስ ገበያ ለመሸፈን የተያዘው ማሻሻያ አካል መሆኑ ኢቲቢዝነስ ቪዉ ከምንጮቿ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

የገንዘብ ሚኒስቴር እና ብሔራዊ ባንክ የሚያጸድቁት ይህ መመሪያ፣ የመንግሥት ሴኩሪቲዎች አሰጣጥን ግልጽ እና ሊተነበይ የሚችል የዕዳ ገበያን ለማጎልበት ያለመ ነው።

በ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ደግሞ የሪፖ ገበያ እንደሚጀመር ተጠቁሟል። ይህ አሰራር የፋይናንስ ተቋማት የመንግሥት ቦንዶችን እንደ መያዣ በመጠቀም የአጭር ጊዜ የገንዘብ እጥረት እንዲቀርፉ ያስችላቸዋል።

በበጀት ዓመቱ የተገመተውን 308.6 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ለመሸፈን እነዚህ የገበያ መሳሪያዎች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይጠበቃል።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories